ሀገሪቱ በፊክስድ ብሮድባንድ ኢንተርኔት ፍጥነት ከዓለም ሁለተኛ ላይ ተቀምጣለች
አረብ ኤምሬትስ በሰኔ ወር በሞባይል የኢንተርኔት ፍጥነት ያለባት ሀገር በመባል ከዓለም ቀዳሚውን ደረጃ ይዛለች።
ሀገሪቱ 204.24 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በማውረድ እና 22.72 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በመጫን በተንቀሳቃሽ ስልክ የኢንተርኔት ፍጥነት ቀዳሚ ሆናለች።
ይህን ያስታወቀው ስፒድ ቴስት የተባለ የኢንተርኔት ተደራሽነት መለኪያዎችና ትንተና አቅራቢ ነው።
በዝርዝሩ መሰረት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በ2023 የመጀመሪያ አጋማሽ በዓለም አቀፍ ደረጃ አንደኛ ሆናለች ሲል ዋም ዘግቧል።
ሀገሪቱ በሚያዝያ ወር ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣ ነበር።
አረብ ኢምሬትስ ቋሚ የብሮድባንድ (በፊክስድ ብሮድባንድ ኢንተርኔት) ፍጥነት በሰኔ ወር ከዓለም ሀገራ መካከል ሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችላለች።
ቋሚ የብሮድባንድ (በፊክስድ ብሮድባንድ ኢንተርኔት) ፍጥነት በቀጠናው ደረጃና ከአረብ ሀገራት መካከል አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
ፊክስድ ብሮድባንድ ኢንተርኔት ፍጥነት በ247.29 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ ፍጥነት ሲንጋፖር ቀዳሚዋ ሀገር ሆናለች።