በመካከለኛው ምስራቅ ማቋረጥ የሰጉ አየርመንገዶች በአፍጋኒስታን በኩል እያለፉ ነው ተባለ
የአየርመንገዶቹ ይህን እርምጃ የጀመሩት እስራኤል እና ኢራን የሚሳይል እና የድሮን ተኩስ ከተለዋወጡበት ከሚያዝያ ወር አጋማሽ ጀምሮ ነው
የሀማስ የፖለቲካ መሪ ሀኒየህ መገደል በመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት ፈጥሯል
በመካከለኛው ምስራቅ ማቋረጥ የሰጉ አየርመንገዶች በአፍጋኒስታን በኩል እያለፉ ነው ተባለ።
የሲንጋፖር አየርመንገድ፣ ብሪቲሽ አየርዋይስ እና የጀርመኑ ሉፎታንዛ አሁን ላይ በመካከለኛው ምስራቅ ባለው የጸጥታ ስጋት ምክንያት በአንጻራዊነት የተሻለ ደህንነት ባለበት በአፍጋኒስታን በኩል የሚያደርጉትን በረራ ጨምረዋል።
እነዚህ አየር መንገዶች በእስያ እና በአውሮፓ በመካከል ባለው ረጅም መንገድ መብረረ ያቆሙት ታሊባን ሀገሪቱን ከተቆጣጠረ እና የአየር ትራፊክ ቁጥጥር ከቆመበት ከሶስት አመት በፊት ነበር።
የአየር ትራፊክ ቁጥጥር አገልግሎቶች ባይጀመሩም፣ ከፍተኛ ስጋት ካለበት በእስራኤል እና በኢራን መካከል ካለው አየር ጋር ሲነጻጸር የአፍጋኑ የተሻለ ነው። የሩሲያ- ዩክሬን ጦርነት በፈረንጆቹ የካቲት 2022 መጀመሩን ተከትሎ ሩሲያ ለአብዛኞቹ የአውሮፓ ሀገራት የአየር ክልሏን ስለዘጋች አብዛኞቹ መስመራቸውን በኢራን እና በመካከለኛው ምስራቅ በኩል ቀይረዋል።
"ግጭቶች የእየተፈጠሩ ሲመጡ፣ የትኛውን የአየር ክልል እንጠቀም የሚለው ስሌት ይቀየራል። በእስራኤል እና ኢራን መካከል ውጥረት በመከሰቱ፣ አየርመንገዶች በተቻለ መጠን አደጋን ለማስወገድ በአፍጋኒስታን አየር ክልል መብረርን ደህነቱ የተጠበቀ አድርገውታል" ሲሉ የፍላይት ራዳር24 ቃል አቀባይ ላን ፔትቸንኪ ተናግረዋል።
የአየርመንገዶቹ ይህን እርምጃ የጀመሩት እስራኤል እና ኢራን የሚሳይል እና የድሮን ተኩስ ከተለዋወጡበት ከሚያዝያ ወር አጋማሽ ጀምሮ ነው።
ከእዚያን ጊዜ ጀምሮ የሲንጋፖር አየርመንገድ፣ የብሪቲሽ አየርዌይስ፣ ሉፍታንዛ እና ሌሎችም አየር መንገዶች በአፍጋኒስታን የአየር ክልል የተወሰኑ መረራዎችን ማድረግ ጀመሩ። ነገርግን የበረራ ቁጥሩ የጨመረው፣ የሀማስ የፖለቲካ መሪ እስማኤል ሀኒየህ በሀምል መጨረሻ መገደሉ ከፍተኛ ቀጣናዊ ውጥረት ካስከተለ ወዲህ ነው።
"በአየር መንገዳችን ትንተና ላይ ጥገኞች ነን። በየጊዜው እበራለሁ፣ ግጭት ባለበት ቀጣና ማብረር ያለውን ስሜት አልወደውም፤ ምክንያቱም ምን እንደሚፈጠር አታውቀውም" ፓይሌት እና የአውሮፓ የኮክፒት ማህበር ኃላፊ ኦትጃን ዲ ብሩይን ተናግሯል።
ሀኒየህን በመግደል እስራኤልን ተጠያቂ ያደረጉት ሀማስ እና ኢራን፣ እስራኤልን እንበቀላለን ሲሉ ዝተዋል።
የሀኒየህ ግድያ በቀጣናው ያለውን ውጥረት ወደ ከፍተኛ ደረጃ ያደረሰው ሲሆን ቀጣናዊ ግጭት ይነሳል ተብሎም ተሰግቷል።