አል አይን ኒውስ አለም አቀፍ ተደራሽነቱን ለማስፋት እየሰራ ነው ሲሉ የአል ዐይን ኒውስ ዋና አዘጋጅ ተናገሩ
አል አላዊ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚዲያ ዘርፉ የተጋረጡበትን ፈተና ለመፍታት ኮንግረሱ ትልቅ ድርሻ አለው ብለዋል
በአቡ ዳቢው ኮንግረስ ተደራሽነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ምክክሮች ተደርገዋል ብለዋል
አል አይን ኒውስ አለም አቀፍ ተደራሽነቱን ለማስፋት እየሰራ ሲሉ የአል ዐይን ኒውስ ዋና አዘጋጅ ተናገሩ፡፡
በአቡ ዳቢ በተካሄደው አለም አቀፍ የሚዲያ ኮንግረስ ላይ የተሳተፉት ዋና አዘጋጁ አህመድ ሰኢድ አል አላዊ፣ አል አይን ኒውስ በተለያዩ ቋንቋዎች ተደራሽነቱን እያሰፋ መሆኑን ተናግረዋል።
በአለም አቀፍ ደረጃ የሚዲያ ዘርፉ የተጋረጡበትን ፈተና ለመፍታት ኮንግረሱ ትልቅ ድርሻ አለው ብለዋል።
በፈረንጆቹ 2015 የተቋቋመው አል አይን ኒውስ በድረ ገፅ አለም አቀፍ ተደራሽነቱን እያሰፋ እንደሚገኝ የገለጹት አል አላዊ አል ዐይን ኒውስ በአለም ዙሪያ ባሰማራቸው ጋዜጠኞቹ ትኩስ አለም አቀፋዊ መረጃዎችን እያደረሰ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ እድሪስ ከአይኤምአይ ዋና ስራ አስፈጻሚ ናርት ብራውን እና ከአል ዐይን ኒውስ ዋና አዘጋጅ ጋር ከአለምአቀፍ የሚዲያ ኮንግረሱ ጎን ለጎን ተወያይተዋል፡፡
አል ዐይን ኒውስ በኢንተርናሽናል ሚዲያ ኢንቨስትመንት ግሩፕ (አይኤምአይ) ውስጥ ያለ አንድ ፕላትሮርም ነው፡፡
ዋና መቀጫውን በአረብ ኢምሬትስ አቡዳቢ ያደረገው አል ዐይን ኒውስ፣ በአረብኛ፣ ፋርስኛ፣ ቱርክኛ፣ ፈረንሳይኛ እና አማርኛ ቋንቋ መረጃዎችን መረጃችን እያሰራጨ ነው፡፡
ዋና አዘጋጁ እንደገለጹት በአቡ ዳቢ እየተካሄደ ባለው ጉባኤም ይህንኑ ተደራሽነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ምክክሮች ተደርገዋል፡፡
በዚሁ ምክክር አለም አቀፍ ሃሳብ አፍላቂ ምሁራን እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ በሚዲያው ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች እየተሳተፉበት መሆኑም ዘርፉ የሚመራበትን ልዩ አካሄድ ለማመላከት ያግዛል ብለዋል።
በኮንገረሱ የጋዜጠኝነት ሙያ የተጋረጡበትን ከስነምግባር ጋር የተያያዙ አደጋዎች በተመለከተም ባለሙያዎች መፍትሄን እንደሚያመላክቱበት ዋና አዘጋጁ ተናግረዋል።