አረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በነገው እለት ሩሲያን ይጎበኛሉ
ፕሬዝዳንት ቢን ዛይድ በሞስኮ ቆይታቸው ከቭላድሚር ፑቲን ጋር በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል
የኢምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሩሲያን እንደ ስትራቴጂክ አጋር ማየታችን ኩራት ይሰማናል ብለዋል
አረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በነገው እለት ሩሲያን እንደሚጎበኙ ተገለጸ፡፡
ፕሬዝዳንቱ በጉብኝታቸው ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን በመገናኘት አረብ ኢምሬትስ እና ሩሲያ መካከል ስላለው ያለውን ወዳጅነትና ግንኙነት እንዲሁም በተለያዩ አህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት እንደሚያደርጉ የኤምሬትስ የዜና አገልግሎት ዘገባ ያመለክታል፡፡
የኤምሬትስ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከሩሲያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ትሰጣለች ብለዋል፡፡
ሀገራቸው “የሩሲያ ፌዴሬሽንን እንደ ስትራቴጂካዊ አጋር እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጓደኛ አድርጋ በማየቷ ኩራት ይሰማታል” ሲሉም አክለዋል ሚኒስትሩ፡፡
ጉብኝቱ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ከዓለም አቀፉ ዲፕሎማሲ መድረክ እየተገለለች ላላቸው ሞስኮ ትልቅ ትርጉም አለው ተብሏል፡፡
ሩሲያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በዩክሬን ጉዳይ ላይ ላንጸባረቀቸው ሚዛናው አቋም እንደምታመሰግን የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከወራት በፊት በሞስኮ ጉብኝት ላደረጉት የኢሚሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ አብደላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን መግለጻቸውም አይዘነጋም፡፡
ሀለቱም ሀገራት በተለያዩ መስኮች ዘርፈ ብዙ ትብብር እንደሚያደርጉ ይተወቃል፡፡
በተለይም የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከዓረቡ ዓለም ያደገች ሀገር እንደመሆኗ ሞስኮ-አቡዳቢ ጋር የምታደርገው ትብብር የጎላ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ በሀገራቱ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ መጠን ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ደርሷል፡፡