የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ከአይኤምአይ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጋር ተወያዩ
የኤይኤም አይ ግሩፐ ዋና ስራ አስፈጻሚ ናርት ብራውን በኢትዮጵያ ያለውን የሚዲያ ስራ አጠናከረው እንደሚቀጥሉ ተናረዋል
ዋና ስራ አስፈጻሚው በሚዲያ ዘርፍ ያለው ትብብር እንደሚቀጥል እና ወደኢትዮጵያም እንደሚመጡ ተናግረዋል
የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ እድሪስ ኢንተርናሽናል ሚዲያ ኢንቨስትመንት ግሩፕ(ኤይኤም አይ) ዋና ስራ አስፈጻሚ ናርት ብራውን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ዋና ዳይሬክሩ በአረብ ኢምሬትስ አቡዳቢ እየተካሄደ ባለው አለምአቀፍ የሚዲያ ኮንግረስ ላይ ተሳትፈዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መሀመድ እድሪስ ከስብሰባ ጎንለጎን ከአይኤምአይ ዋና ስራ አስፈጻሚ በተጨማሪ ከአል ዐይን ኒውስ ዋና አርታኢ ሰኢድ አል አላዊ ጋርም ተወያይተዋል፡፡
አቶ መሀመድ በአይኤም አይ ግሩፕ ስር ባሉት በስካይ ኒውስ አረብኛ እና በአማርኛ የኢትዮጵያን እውነታ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለይም ለአረቡ አለም ለማድረስ የሚያደርጉትን ጥረት ኢትዮጵያ እንደምታደንቅ በወይይቱ መግለጻቸውን ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ያለውን እድል በመጠቀም የኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤሚርትስ ግንኙነትን ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም መወያየታቸውን አንስተዋል ዳይሬክተሩ፡፡
አል አይን በአማርኛ እና አረብኛ ቋንቋ በቀጣይም የኢትዮጵያን ትክክለኛ ገፅታ ለአለም ተደራሽ እንዲያደርግ የሚያስችል ምክክር ማድረጋቸውን ያነሱት አቶ መሀመድ፥ የኢትዮጵያ መንግስት ተገቢውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁነቱንም አረጋግጠዋል።
ኤይኤም አይ ግሩፐ በኢትዮጵያ ተደራሽነቱን እንዲያሰፋም መጋበዙን ገልጸዋል፡፡
ግሩፑ በኢትዮጵያ የሚገኙ መገናኛ ብዙሃንን በስልጠናና በአቅም ግንባታ እንዲያግዝ መጠየቃቸውንና አዎንታዊ ምላሽ ማግኘታቸውንም አብራርተዋል።
የኤይኤም አይ ግሩፐ ዋና ስራ አስፈጻሚ ናርት ብራውን በኢትዮጵያ ያለውን የሚዲያ ስራ አጠናከረው እንደሚቀጥሉ ተናረዋል፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚው በሚዲያ ያለው ትብብር እንደሚቀጥል እና ወደኢትዮጵያም እንደሚመጡ ተናግረዋል፡፡
የአል ዐይን ኒውስ ዋና አዘጋጅ ሰኢድ አል አላዊ የኢዮጵያ ሚዲያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክትር ጋር በመገናኘታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ዋና አዘጋጁ የኢትዮጵያን ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘፍር ለመርዳት እንደሚጥሩ ገልጸዋል፡፡