የሳኡዲው ክለብ የሞሮኮውን ግብ ጠባቂ ያሲን ቦኑን አስፈረመ
በዚህ ሳምንት አል ሂላል ብራዚላዊውን አጥቂ ኔይማርን ከፈረንሳዩ ፖራስ ሴንት ጀርሜን(ፒኤስጂ) አስፈርሟል
አል ሂላል ሞሮኳዊውን ግብ ጠባቂ ያሲን ቦኑን ከስፔኑ ሲልቫ ክለብ ለሶስት አመት ማስፈረሙን የሳኡዲ ኘሮሊጉ ክለብ አስታውቋል
አል ሂላል ሞሮኳዊውን ግብ ጠባቂ ያሲን ቦኑን ከስፔኑ ሲልቫ ክለብ ለሶስት አመት ማስፈረሙን የሳኡዲ ኘሮሊጉ ክለብ አስታውቋል።
"የአትላንቲኩ አንበሳ የኛ ግብ ጠባቂ" ሆኗል ሲል አል ሂላል በኤክስ ወይም ቀደም ሲል ቲዊተር በሚባለው ማህበራዊ ገጹ ላይ ገልጿል።
የስምምነቱ ዝርዝር ይዘት ይፋ ባይሆንም የስፔን ሚዲያዎች ሲልቫ 22.8 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቱን ዘግበዋል።
አል ሂላል እንደገለጸው ስምምነቱን በገንዘብ የረዱት የክለብ የክብር አምባሳደር ፕሪንስ አል ዋለድ ቢን ታላል ናቸው።
የ32 አመቱ ያሲን ቦኑ የስፔኑ ሲልቫ ክለብ የመጀመሪያ ምርጫ ግብ ጠባቂ ሲሆን ሲልቫ ሁለት የአውሮፖ ሊግ ዋንጫዎችን እንዲያገኝ እና ሀገሩ ሞሮኮ ደግሞ በኳታሩ የአለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ እንድትደርስ አስችሏል።
በተለምዶ ቦኖ እየተባለ የሚጠራው ቦኑ በባየር ሙኒክ እና በሪያል ማድሪድም እንደሚፈለግ የሚያመለክቱ መረጃዎች ወጥተዋል።
በሳኡዲ አረቢያ እና በእስያ እጅግ ስኬታማ የሆነው አል ሂላል 18 የሀገር ውሰጥ ዋንጫዎችን እና አራት የእሲያ ሻምፒዎንስ ሊግ ድሎችን ጨምሮ 66 ውድድሮችን አሸንፏል።
በዚህ ሳምንት አል ሂላል ብራዚላዊውን አጥቂ ኔይማርን ከፈረንሳዩ ፖራስ ሴንት ጀርሜን(ፒኤስጂ) አስፈርሟል።
ፖርቱጋላዊውን አሰልጣኝ ጆርጅ ጀሰስን በድጋሚ ለአንድ አመት ያስፈረመው አል ሂላል በሳኡዲ ፕሮሊግ ሁለተኛ ዙር ውድድር አል ፌኢሃን በመጭው ቅዳሜ ያስተናግዳል።