አውሮፕላን ለመከስከስ የሞከረው አብራሪ በ83 ሰዎች ግድያ ክስ ተመሰረተበት
አብራሪው የአላስካ አየር መንገድ ሰራተኛ ነበር ተብሏል
የግለሰቡ ድርጊት ተደርሶበት እንዲታሰር ሲደረግ አውሮፕላኑ ወደ ኦሪጎን እንዲበር ማድረግ መቻሉ ተገልጿል
አውሮፕላን ለመከስከስ የሞከረው አብራሪ በ83 ሰዎች ግድያ ክስ ተመሰረተበት።
ጆሴፍ ዴቪድ ኤመርሰን ንብረትነቱ የአሜሪካው አላስካ አየር መንገድ ሰራተኛ ሲሆን የአውሮፕላን አብራሪም ነበር።
ግለሰቡ ከዋሸንግተን ወደ ሳንፍራንሲስኮ 80 መንገደኞችን አሳፍሮ እየተጓዘ ባለ አውሮፕላን ውስጥ አደጋ ለመፍጠር ሞክሮ እንዳልተሳካለት ተገልጿል።
ይህ አብራሪ በአውሮፕላኑ ውስጥ ተሳፍሮ እየተጓዘ የነበረው በእረፍት ቀኑ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን የተሳፈረበትን እና የሚሰራበትን አውሮፕላን ለመከስከስ ሲጥር ተይዟል ተብሏል።
ይህ በእረፍት ላይ የነበረው አብራሪ የአውሮፕላኑን ሞተር በማጥፋት እንዲከሰከስ በእንቅስቃሴ ላይ እያለ በስራ ባልደረቦቹ ተይዞ እንዲታሰር መደረጉን ቢቢሲ ዘግቧል።
አብራሪው በአውሮፕላኑ ላይ ተሳፍረው የነበሩ 83 ሰዎችን ደህንነት አደጋ ላይ በመጣል የግድያ ክስ ተመስርቶበታል ተብሏል።
አውሮፕላኑም ለተሳፋሪዎቹ አስቸኳይ የህክምና ጉዳይ አግልጥሟል በሚል ካሳወቀ በኋላ በ15 ደቂቃ ውስጥ ወደ መሬት እንዲያርፍ መደረጉ ተገልጿል።
በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ መንገደኞች ይህ ሁሉ ሲሆን መረጃ እንዳልነበራቸው እና የአውሮፕላኑ አብራሪ የተፈጠረውን ክስተት የተቆጣጠረበት መንገድ አድናቆት አስችሮታል ተብሏል።