አረብ ኤምሬትስ “እስራኤልን ለመደገፍ የአሜሪካ አውሮፕላኖች አየር ክልሌ ውስጥ አልገቡም” አለች
አረብ ኤምሬትስ እስራኤልና ሀማስ ግጭት እንዲያቆሙ መጠየቋ ይታወሳል
አረብ ኤምሬትስ የአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ለእስራኤል ድጋፍ ለመስጠት አል ዳፍራ አየር ማረፊያ ገቡ መባሉን መሰረተ ቢስ ነው ብላለች
አረብ ኤምሬትስ “እስራኤልን ለመደገፍ የአሜሪካ አውሮፕላኖች አየር ክልሌ ውስጥ አልገቡም” አለች።
አረብ ኤምሬትስ መከላከያ ሚንስቴር የአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ለእስራኤል ድጋፍ ለመስጠት በሀገሪቱ አል ዳፍራ አየር ማረፊያ አረፈ መባሉን አስተብሏል።
ሚንስቴሩ በአንዳንድ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኸን ሲሰራጭ የነበረውን ውንጀላ መሰረተ ቢስ በማለት ነው ያስተባበለው።
የመከላከያ ሚንስቴር በቀድሞው ትዊተር በአሁኑ ኤክስ ባወጣው መግለጫ ክሱ መሰረተ ቢስ መሆኑን ተናግሯል።
ሚንስቴሩ እንዳብራራው የአሜሪካ አውሮፕላኖች በአል ዳፍራ ጣቢያ መገኘት በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው ወታደራዊ ትብብር መሰረት ለበርካታ ወራት አስቀድሞ የተያዘ ነው።
በመሆኑም ያለው የአረብ ኤምሬት መከላከያ ሚንስቴር ከእስራኤል ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ገልጿል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እስራኤልና ሀማስ ንጹሃንን አደጋ ላይ ከሚጥሉ እርምጃዎች በመቆጠብ ግጭት እንዲያቆሙ ጠይቃለች።
የአረብ ኤምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተፋላሚዎቹ ወገኖች ለንጹሃን ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት ግጭት ሊያቆሙ እንደሚገባ ነው ያሳሰበው።
ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ፥ “ሃማስ ንጹሃን ወደሚገኙባቸው የእስራኤል ከተሞችና መንደሮች በሺዎች የሚቆጠሩ ሮኰቶችን መተኮሱ አደገኛ ነው፤ ውጥረቱንም ያንረዋል” ብሏል።
ሃማስ ባሳለፍነው ቅዳሜ በእስራኤል ላይ ያለተጠበቀ እና ድንገተኛ ጥቃት መሰንዘረሩን ተከትሎ በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል የተጀመረው ጦርነት ዛሬ ሰባተኛ ቀኑን ይዟል።
በሃማስ ጥቃት እና በእስራኤል የአየር ድብደባ ከሁለቱም ወገኖች የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ2 ሺህ 800 ማለፉ ተነግሯል።