ከእስራኤል አቻው ጋር አልወዳደርም ያለው አልጀሪያዊው የጁዶ ስፖርተኛ ለ10 ዓመት ታገደ
ስፖርተኛው የታገደው ከእስራኤል አቻው ጋር አልወዳደርም በማለቱ ነው
ፈቲህ ኑሪን የተሰኘው አልጀሪያዊው ራሱን ያገለለው በቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ ነበር
የእስራሉን ተወዳዳሪ አልገጥምም በሚል ራሱን ያገለለው የጁዶ ስፖርተኛ ለ10 ዓመት ታገደ።
ፈቲህ ኑሪን የአልጀሪያ ዜግነት ያለው የጁዶ ስፖርተኛ ነበር።
ሀገሩን ወክሎ ከአንድ ወር በፊት በተጠናቀቀው የቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ በጁዶ ስፖርት ለመወዳደር ወደ ጃፓን አምርቶም ነበር።በዚሁ ውድድር ላይ ሀገሩን ወክሎ ወደ ስፍራው ያቀናው የአስራኤሉ የጁዶ ስፖርተኛ ከአልጀሪያው አቻ ስፖርተኛ ጋር መወዳደር ነበረባቸው።
ይሁንና የአልጀሪያው ተወዳዳሪ ከእስራኤል አቻው ጋር መወዳደር እንደማይችል በመግለጽ ውድድሩን አቋርጧል።
ስፖርተኛው የአልጀሪያ አቻውን ላለመግጠሙ የወሰነው እስራኤል በፍልስጤማዊያን ሙስሊሞች ላይ በደል ታደርሳለች በሚል ነበር።
ዓለም አቀፉ የጁዶ ስፖርት ፌዴሬሽን በበኩሉ ጉዳዩ ስፖርት ከማንኛውም ፖለቲካ ነጻ እና ገለልተኛ መሆን አለበት የሚለውን ህግ የሚጥስ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ብሏል።በዚህም መሰረት የአልጀሪያው ስፖርተኛ ይሄንን ህግ ጥሷል በሚል ለ10 ዓመት ያህል ከስፖርታዊ ውድድሮች ማገዱን አስታውቋል።
አልጀሪያዊው የጁዶ ስፖርተኛ በቤጂንግ ኦሎምፒክ ውድድር ላይ የብር ሜዳሊያ ለአገሩ አስገኝቶ ነበር።
ሱዳናዊው የጁዶ ተወዳዳሪ በዚሁ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ ከእስራኤል አቻው ጋር ውድድር እያለበት አስቀድሞ በጉዳት ምክንያት ከውድድሩ ራሱን ማግለሉን ተከትሎ ዓለም አቀፉ የጁዶ ፌዴሬሽን ከእስራኤል መንግስት ጋር በተደረገ ድርድር መፈታቱ ተገልጿል።
ከሁለት ዓመት በፊት ኢራናዊው ስፖርተኛ ከአስራኤል አቻ ተወዳዳሪው ጋር አልወዳደርም በሚል ራሱን ማግለሉን ተከትሎ የ4 ዓመት እገዳ እንደተጣለበት ይታወቃል።