ከሀገሪቱ ዋና ከተማ አልጀርስ በስተምስራቅ በሚገኙ መንደሮች የተከሰተውን እሳት ያስነሱት አቀጣጣዮች መሆናቸው ተገልጿል
በአልጄሪያ በደን ውስጥ በተነሳ የሰደድ እሳት የ42 ሰዎች ህይወት ማፉን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
በሰደድ እሳቱ 25 የሀገሪቱ ወታደሮችን ጨምሮ 42 ሰዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቀዋል።
ከሀገሪቱ ዋና ከተማ አልጀርስ በስተምስራቅ በሚገኙ መንደሮች በተከሰተው በዚህ የእሳት አደጋ ነዋሪዎችን ለማዳን ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ወታደሮች ህይወትም አልፏል።
የአልጀሪያ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ካሜል ቤልጃውድ እሳቱን ያስነሱት አቀጣጣዮች መሆናቸውን ቢገልጹም ዝርዝር ጉዳይ ከመናገር ግን ተቆጥበዋል ነው የተባለው። በዚህ መንገድ እሳቱ የተነሳ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ከዛ በኋላ ግን እሳቱ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ገልጸዋል፡፡
እሳቱን በማስነሳት የሚጠረጠሩ ዜጎች እንደሚያዙም ሚኒስትሩ ገልጸዋል። በሀገሪቱ ካቢሌ የሚባለው አካባቢ ነዋሪዎች እሳቱን ለማጥፋት የዛፍ ቅጠሎችን ሲጠቀሙ እንደነበር ተዘግቧል።
የአልጀሪያ መከላከያ ሚኒስቴር በርካታ ወታደሮች እሳቱን ለማጥፋት ባደረጉት ጥረት መቃጠላቸውን ገልጿል።
በዚህ የእሳት አደጋ የግለሰቦች መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸው የተገለጸ ሲሆን፤ የሀገሪቱ መንግስትም የሟቾች ቁጥር 42 መድረሱን ይፋ አድርጓል።
የአልጄሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር አይማን ቤናብድርሃማኔ በእሳት አደጋው የ25 ወታደራራዊ ሰዎች ህይወት ማለፉንም አስታውቀዋል።