በአየር ንብረት ለውጥ ውጊያ ብልጫ ያለው አልሙኒየም
የአውቶሞቢል ኢንዱስትሪው በተለያዩ ዘርፎች እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ተመክሯል
አልሙኒየም በኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ላይ መጠቀም የካርበን ልቀተን ወደ ዜሮ የማድረስ ጉዞን ያግዛል
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በልቀት ረገድ ዜሮ ቢሆኑም፤ ተሽከርካሪዎቹን ለማምረት ግን ሁሉም ሰው ከሚያስበው በላይ ከባቢን ይጎዳሉ።
ስለዚህም ዜሮ ካርቦን የሆነው አልሙኒየም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ስሪት በመቀየር፤ የአውቶሞቢል ኢንዱስትሪውን ወደ አረንጓዴ ይቀይራል።
ልቀትን ዜሮ የማድረስ ግስጋሴን ለመምራት፤ አርቆ አሳቢ ባለድርሻዎች ቁሳቁስን በመምረጥ፣ ተረፈ ምርትን ለዳግም አገልግሎት ለማዋል፣ ለግልጸኝነትና ለተጠያቂነት በትብብር መስራት አለባቸው።
ዓለም ተሽከርካሪዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ለመቀየር ሽግግር እያደረገች ሲሆን፤ ልቀታቸው ዜሮ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን ማምረት ግን ትልቁ እክል እንደሚሆን የሚጠበቅ ነው።
ምንም እንኳ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ግልጋሎት ላይ ሲውሉ ከባቢን በካይ ልቀት ባይኖራቸውም፤ ከአየር ንብረት ለውጥ ግን ንጹህ አይደሉም።
እያንዳንዱ ተሽከርካሪ ከ50 ሽህ በላይ ክፍሎች የሚሰራ ሲሆን፤ ሁሉም የተሽከርካሪ ክፍሎች ታዲያ ሲመረቱ ለልቀት የራሳቸው ሚና አላቸው።
ይህም ማለት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ከልቀት ነጻ ለመሆን እነዚህ ክፍሎች አልቀት ነጻ መሆን አለባቸው።
ፓትዌይ የተባለ ድርጅት ሪፖርት 1.5 ድግሪ ውጥንን ለማሳካት የአውቶሞቢል ኢንዱስትሪው በተለያዩ ዘርፎች እርምጃ መውሰድ አለበት።