በአየር ንብረት ለውጥ ክፉኛ እየተጎዱ ያሉ እነማን ናቸው?
በእድሜ የገፉ ሰዎች፣ ሴቶችና አካል ጉዳተኞች ክፉኛ እየተጎዱ ነው
ከሙቀት ጋር በተያያዘ እድሜያቸው 65 እና ከዚያ በላይ ባሉ ሰዎች የሚመዘገበው የምት ቁጥር በእጥፍ ጨምሯል
ምንም እንኳ በአየር ንብረት ለውጥ በሁሉም ሰው በተወሰነ መጠን ተጽዕኖ ቢደርስም፣ በእድሜ የገፉ ሰዎች፣ ሴቶችና አካል ጉዳተኞች ክፉኛ እየተጎዱ ነው።
በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየደረሰ ባለው ከባድ የአየር ሁኔታ መጨመርና መስፋፋት የዓለም ህዝብ እያረጀ ነው። ይህም ከባድ ችግር ደቅኗል።
በ2030 በዓለም ከስድስት ሰዎች አንዱ 60 ዓመትና በላይ ይሆናል።
የዚህ እድሜ ክልል ቡድን ከ1.4 በሊዮን በ2050 ወደ 2.1 በሊዮን እንደሚያደርግ ይገመታል።
ይሁን እንጂ በርካታ በእድሜ ጠና ያሉ ሰዎች ተጽዕኖውን ለመቀልበስ ወይም ለመቀነስ የአካል፣ የስነ-ልቦና፣ ማህበራዊና የገንዘብ አቅም የላቸውም። ይህ በሰፊው የሚስተዋለው በደቡብ የዓለም ክፍል ነው።
አረጋዊያን በእድሜያቸው ምክንያት ሰውነታቸው ሙቀትን መቆጣጠር አቅሙ ስለሚቀንስ የሙቀት ማዕበሎች ክፉኛ ይጎዷቸዋል። እንደ መተንፈሻ፣ የልብ ህመምና ስኳር ያሉ ተላላፊ ያልሆኑ (ክሮኒክ) በሽታዎች ላይ ተጽዕኖው ብርቱ ነው።
ባለፉት ሁለት አስርት ዓመት ከሙቀት ጋር በተያያዘ እድሜያቸው 65 እና ከዚያ በላይ ባሉ ሰዎች የሚመዘገበው የምት ቁጥር በእጥፍ ጨምሯል።
በ2018 ሙቀት ጋር የተያያዘ ሞት 300 ሽህ ደርሷል። በ2022 የበጋ ወቅት በአውሮፓ እድሜያቸው ከ65 እስከ 79 ያሉ ከዘጠኝ ሽህ በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ከ80 በላይ የሆናቸው ደግሞ 37 ሽህ የሚሆኑ ሰዎች ከሙቀት ጋር በተያያዘ እክል ሞተዋል።