ኢትዮጵያና አረብ ኤምሬትስ ዘላቂነት የአየር ንብረት ጉዳዮች ላይ…
ኢትዮጵያና አረብ ኢምሬትስ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና በ2050 ልቀትን ዜሮ ለማድረግ ፍላጎትና ራዕይ ይጋራሉ።
ኢትዮጵያና አረብ ኤምሬቶች በቅርብ ጊዜያት በታዳሽ ኃይል ዘርፍ የተለያዩ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል
ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና በ2050 ልቀትን ዜሮ ለማድረግ ፍላጎትና ራዕይ ይጋራሉ።
ይህም ሁለቱ ሀገራት ዘላቂ ከባቢና የአየር ንብረት ለውጥን ለመተግበር ያላቸው ፍላጎት ማዕቀፍ አካል ነው።
የታዳሽ ኃይል ብዝኃነትን በማሳደግ፣ ባህላዊ የኃይል ምንጮች ላይ ካለው ጥገኝነት በመላቀቅና የግሪን ሀውስ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ ስልታዊ ውጥን ይዘዋል።
ኢትዮጵያ የድርሻዋን በአየር ንብረት ለውጥ እርምጃውን ማጠናከር ላይ ትሰራለች።
ሀገሪቱ ይህን ለማድረግም በርካታ ብሄራዊ ስልቶችንና እርምጃዎችን በመለየት በማዕቀፉ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ አበርክቶዋን ትወጣለች።
እንደ ኤምሬትስ የዜና ወኪል ዘገባ ኢትዮጵያ በዱባይ በሚካሄደው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 28) በደስታ እየጠበቀች ነው።
ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በቅርብ ጊዜያት በታዳሽ ኃይል ዘርፍ የተለያዩ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።
በዓለም የታዳሽ ኃይል መሪ የሆነው 'አቡዳቢ ፊውቸር ኢነርጂ' በጸሀይ ኃይል ኢትዮጵያን መደገፉ ይቀጥላል ተብሏል።
በ2021 በኢትዮጵያ ከጸሀይ ኃይል 500 ሜጋዋት ኃይል ለማመንጠት ስምምነት ተደርሷል።