
ውሻው ተቀባበሎ የተቀመጠውን መሳሪያ ሲተኩስ አሳዳጊው ተኝቶ ነበር ተበሏል
በአሜሪካ አንድ ውሻ መሳሪያ ተኩሶ አሳዳጊውን ማቁሰሉን ፖሊስ አስታወቀ።
ፖሊስ ባሳለፍነው ረቡዕ እንዳስታወቀው ከሆነ ውሻው ከአልጋ ላይ ዘሎ በሚወርድበት ጊዜ ተቀባብሎ የተቀመጠ ሽጉጥ ቃታ ላይ በመርገጡ ነው መሳሪያው የተተኮሰው።
በውሻው በተተኮሰው ሽጉጥም አሳዳጊው መቁሰሉን ፖሊስ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
የቲኒዟ ሙምፊስ ነዋሪ የሆነው ግለሰብ ሽጉጡ በሚተኮስበት ወቅት ከትዳር አጋሩ ጋር ተኝቶ የነበረ ሲሆን፤ የግራ ታፋው ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሶበት በሆስፒታል ህክምና እንደተደረገለት ፖሊስ ገልጿል።
ውሻው እንዴት መሳሪያውን ሊተኩስ ቻለ? ሊሚለው ጥያቄም ፖሊስ በሰጠው ምላሽ “ውሻው ከአልጋ ላይ እየዘለለ እየተጫወተ ነበር፤ በዚህ ወቅትም ተቀባብሎ የነበረ መሳሪያ ቃታ በመርገጡ ተተኩሷል” ብሏል።
ፖሊስ በሪፖርቱ የመሳሪያውን አይነት ባይጠቅስም ሁነቱን “ድንገተኛ አደጋና ጉዳት” ሲል ገልጾታል።
በአሜሪካ ውስጥ በጦር መሳሪያ የሚፈጸሙ ጥቃች በብዛት የሚከሰቱ ቢሆንም፤ እንስሳት በሰው ላይ ተኮሱ የሚለው ግን የተለመደ አይደለም።
ከሁለት ዓመት በፊት በአሜሪካ ካንሳስ የጀርመን ሺፐርድ ውሻ ተቀባብሎ የተቀመጠ የአደን ጠብመንጃ ላይ ድንገት ረግጦ በመተኮሱ የ30 ዓመቱ ሰው ህይወት ማፉ ይታወሳል።
በፈረንጆቹ 2018 ላይም የ51 ዓመቱ አሜሪካዊ በውሻው በተተኮሰ ጥይት እግሩ ላይ መመታቱ ተነግሯል።