የሰለጠነ ውሻ በበሽታ የተጠቁ ዛሮችን ለመለየት ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ ዋለ
ኢቮር የተባለው ውሻ 150 የእጽዋት ዝርያዎችን ሊያጠፉ የሚችሉ አደገኛ የሆኑ 'ፓቶጅኖችን' ወይም ፍላጻዎችን መለየት እንዲችል ሲሰለጥን ቆይቷል
ደን ምርምር በተባለው ተቋም በተመራው ሙከራ ኢቮር የመጀመሪያ ሙከራውን 89 በመቶ አሳክቷል
የሰለጠነ ውሻ በበሽታ የተጠቁ ዛሮችን ለመለየት ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ ውሏል።
እንግሊዝ ውስጥ ውሾች የዛሮችን በሽታ በተሰካ ሁኔታ ለመጀመሪያ ጊዜ በመለየት የሰው ልጅ የልብ ወዳጅ ብቻ አለመሆናቸውን አስመስክረዋል ሲል ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
እንደዘገባው ከሆነ የስድስት አመት እድሜ ያለው ኢቮር የተባለው ውሻ 150 የእጽዋት ዝርያዎችን ሊያጠፉ የሚችሉ አደገኛ የሆኑ 'ፓቶጅኖችን' ወይም ፍላጻዎችን መለየት እንዲችል ሲሰለጥን ቆይቷል።
'ፓይቶፕቶራ ራሞሩም ኦርጋኒዝም' ለጣውላ መስሪያ አስፈላጊው የሆነውን ላርች ዛፍ ጨምሮ መጠነሰፊ ጉዳት ያስከትላል። ለኢቮር የተሰጠው ስልጠና በማሽተት መለየት የሚችልበትን ዘዴ የሚያካትት ነው።
ኢቮር በአፈር፣ በእጽዋት እና በታከመ ውሃ ውስጥ ያለ ፈላጻ በመለየት የመጀመሪያውን ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ አልፏል። በሁለተኛው ዙር የቀረበው ፈተና አዲስ የሰራ አካባቢ ማስተዋወቅ ሲሆን ኢቮር ፓይቶፕቶራ ራሞሩም የተባለው የዛፍ በሽታ ከሌሎች የፓይቶፕቶራ አይነቶች በተሳካ ሁኔታ መለየች ችሏል። ደን ምርምር በተባለው ተቋም በተመራው ሙከራ ኢቮር የመጀመሪያ ሙከራውን 89 በመቶ አሳክቷል።
በተቋሙ የደን ተመራማሪ ፖቶሎጂስት የሆኑት ዶክተር ሂዘር ዱን የሙከራ ውጤቱ "በእጅጉ የሚያበረታታ እና ነፍሳትን እና በሽታዎችን ለማጥፋት በምናርደገው ዘመቻ ውሾች ትልቅ አቅም እንዳላቸው ያሳየ ነው"ብለዋል።
ተመራማሪው አክለውም እንዳሉት "ሰነምህዳር አስፈላጊ ነው፤ እንደ ኢቮር ያሉ የሰለጠኑ ውሾችን መጠቀም ዛፎችን ለመከለል የሚረዳ የሚያስደስት አዲስ ዘዴ ነው።"
በኢቮር ላይ የተደረገው ሙከራ ስኬታማ መሆኑን ተከትሎ ደን ምርምሩ የሰለጠኑ ውሾች ሌሎች ነፍሳቶችን እና በሽታዎችን ለመከላከል እንዴት ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ የሚለውን እያጠና ነው ተብሏል።
ይህ ሙከራ የሀገሪቱ መንግስት እየጨመረ የመጣውን የዛፍ በሽታ ለመቀነስ ከወሰዳቸው እርምጃዎች ውስጥ የቅርብ ጊዜ ተደርጎ የሚወረድ ነው።