የጊኒየስ ወርልድ ሪከርድስ ቦቢ የተባለው የዓለም ባለረጅም ዕድሜው ውሻ መሞቱን ይፋ አድርጓል
በዓለም በእድሜ ትልቁ ውሻ ሞተ።
የጊኒየስ ወርልድ ሪከርድስ ቦቢ የተባለው የዓለም ባለረጅም ዕድሜው ውሻ መሞቱን ይፋ አድርጓል። ይህ ውሻ ጠቅላላ እድሜውን ያሳለፈው በማዕከላዊ ፖርቹጋል ሲሆን በ31 አመቱ ሞቷል።
ቦቢ ከፈረንጆቹ 1939 ጀምሮ በአውስትራሊያው በ29 አመት እድሜ ተይዞ የነበረውን በማሻሻል አዲስ ሪከርድ አስመዝግቧል።
የቦቢን መሞት በማህበራዊ ሚዲያ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ ያደረገው የእንስሳት ሀኪም የሆነው ካረን ቤከር ቦቢ 31 አመት ከ165 ቀናት በመኖር ቀደም ሲል ተይዞ የነበረውን ሪከርድ መስበሩን አስታውቋል።
ምንምእንኳን የውሾች በህይወት የመኖር የእድሜ ጣሪያ ከ12 እስከ 14 ቢሆንም ቦቢ በገጠር በመኖሩ እና የሰው ምግብ ሲመገብ በመኖሩ ለብዙ አመታት መቆየት ችሏል። ሊዮነል ኮስታ እና ቤተሰቦቹ ቦቢን በማገዶ እንጨት ክምር ላይ ነበር ያገኙት።
ቦቢ እድሜውን ደስተኛ ህይወት በመኖር ነው ያሳለፈው። ቦቢ ከመሞቱ በፊት እንቅስቃሴ ማድረግ ይመቸዋል፤ ነገርግን እድሜው በመግፋቱ እና እይታው እየቀነሰ በመሄዱ ምክንያት እረፍት ማድረግ ይፈልግ ነበር።
ጊኒየስ ወርልድ ሪከርድስ የቦቢን ታሪክ "ተአምር" ሲል ገልጾታል።