ልጆቼ ትኩረት አልሰጡኝም ያሉ ወላጅ ንብረታቸውን ለውሻቸው አወረሱ
የሶስት ልጆች እናት የሆኑት ወላጅ ውሻቸውን የ2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር ወራሽ አድርገዋል
እናትየዋ ብዙ የደከምኩላቸው ልጆቼ ስታመምም ሆነ ሲደክመኝ ጠይቀውኝ አያውቁም ብለዋል
ልጆቼ ትኩረት አልሰጡኝም ያሉ ወላጅ ንብረታቸውን ለውሻቸው አወረሱ፡፡
በቻይናዋ ሻንጋይ የሚኖሩ አንድ እናት ሶሶት ልጆች 20 ሚሊዮን ዩዋን ወይም 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ አላቸው፡፡
ልጆቼን በጥሩ ስነምግባር አሳድጌ ለቁም ነገር አብቅቻለሁ የሚሉት እኝህ እናት በምላሹ ግን ልጆቼ እኔን የማይጠይቁ እና የማይንከባከቡ ሆነዋል ብለዋል፡፡
በዚህም ምክንያት ያለኝን ሀብት ሁሌም አጠገቤ ለሚገኘው ውሻዬ አውርሻለሁ ማለታቸውን ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት ዘግቧል፡፡
እናትየዋ አክለውም አሞኝ አልጋ ላይ ለቀናት በህመም ሳሳልፍ አንድም ቀን ብቅ ብለው ጎብኝተውኝ አያውቁም ያሉ ሲሆን ውሻዬ እና ደመቴ ግን ከአጠገቤ ጠፍተው አያውቁም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ያለኝ ንብረት ሁሉ ውሻዬ እና ድመቴ እስከ ህይወታቸው ፍጻሜ ድረስ እንዲኖሩበት እፈልጋለሁ ያሉት እኝህ በልጆቻቸው የተማረሩት እናት ገንዘባቸውን የሚያስተዳድር ጠበቃ፣ እንክብካቤ የሚያደርጉላቸው የእንስሳት ሐኪም እና ሌሎች ባለሙያዎችንም ቀጥረውላቸዋል፡፡
የእናትየውን ሁኔታ የሚገልጸው ይህ ዘገባ ለህዝብ ይፋ ከሆነ በኋላ ጉዳዩ ሚሊዮኖችን ያነጋገረ ሲሆን ወላጆቻቸውን የማይረዱ ልጆች እንዲቀጡ የሚያደርግ ህግ ሊወጣ ይገባል የሚሉ ሀሳቦችም በዘስፋት እየተነሱ ይገኛል፡፡
አንድ ወላጅ ደግሞ “ልጄ እኔን የማትረዳኝ ከሆነ ያለኝን ሀብት ሁሉ ለሌሎች አወርሳለሁ” ስትል ዌቦ በተሰኘው የቻይና ምህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ የጻፈችው አስተያየት ብዙዎች ደግፈውታል፡፡