የቀድሞ የአሜሪካ ወታደር የነበሩት የ90 ዓመት አዛውንት ሞትን እየተጠባበቁበት ባለው አልጋቸው ላይ ሁነው የሁለተኛ ደረጃ ዲፕሎማቸውን ተቀብለዋል
ሪቻርድ ሬምፕ የተባሉት የቀድሞ አሜሪካ ወታደር የሁለተኛውን የአለም ጦርነት መቀስቀስ ተከትሎ በ17 አመታቸው ነበር ትምህርታቸውን አቋርጠው ጦሩን የተቀላቀሉት።
በቬትናም ጦርነት የመድፍ አስተኳሽ የነበሩት አዘዋንቱ ጎን አጥንታቸው ላይ በደረሰባቸው ጉዳት ህክምና ሲከታተተሉ ቆይተው ጉዳቱ ወደ ካንሰር ተቀይሮ አልጋ ከያዙ ሰንበትበት ብለዋል።
- በ83 አመታቸው የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ያገኙት አዛውንት “ለመማር አይረፍድም” ይላሉ
- በ70 ዓመታቸው የመጀመሪያ ዲግሪ ለመማር ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የገቡት አዛውንት
በአዛወንቶች ማቆያ ህክምናቸውን እየተከታተሉ የሚገኙት ሪቻርድ ሬምፕ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ማጠናቀቅ የህይወት ግባቸው እንደነበር ይናገራሉ።
ሰዎች ለፈለጉት ነገር የአላማ ጽናት ካላችው ካንሰርም ሆነ እድሜ አይገድባቸውም የሚሉት እሳቸው በመጨረሻም ከበሽታ ጋር እየተናነቁም ቢሆን ግባቸውን አሳክተዋል።
ሪቻርድ ከመሞታቸው በፊት ህልማቸው እውን በመሆኑም ደስተኛ ነኝ ብለዋል።
በእድሜ ማምሻ በተለይ ከትምህርት ጋር የተያያዘ ህልምን የማሳካት ዜና በርከት ብሎ የሚነገር ነው።
ከዚህ ቀደም በዛው አሜሪካ ማሳቹሴት ፍሬድ በትለር የተባሉ የ106 አመት አዛውንት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ዲፕሎማቸውን ተቀብለዋል።
በተመሳሳይ በቅርቡ በ83 አመታቸው ከሆዋርድ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ስለተቀበሉት ማሪ ፎውለር ሰምተናል።
በወቅቱም በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ሆዋርድ ዩኒቨርሲቲ በ156 አመት ታሪኬ በእድሜ የገፉ ምሩቅ ናቸው ላላቸው የ83 አመቷ ማሪ ፎውለር የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክቱን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሮ ነበር።