ፓርቲው “ማንነትን መሰረት” ባደረገው ጥቃት ላይ መምከሩን ገለጸ
ፓርቲው ”በ12ኛው የአዴፓ ጉባኤ የተያዙ አማራ ህዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ” እየሰራሁ ነው ብሏል
የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ከአርቲስት ሀጫሉ ግድያ በኋላ በተከሰተው “ማንነትን መሰረት” ባደረገው ጥቃት ላይ መምከሩን ገለጸ
የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ከአርቲስት ሀጫሉ ግድያ በኋላ በተከሰተው “ማንነትን መሰረት” ባደረገው ጥቃት ላይ መምከሩን ገለጸ
የአማራ ብልጽግና ፓርቲ በቅርቡ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተፈጸሙ “ማንነትን መሠረት” ባደረጉ ጥቃቶች ላይ ሰፊ ውይይት ማድረጉን በፌስ ቡክ ገጽ አስታውቋል፡፡
የአርቲስቱን ግድያ ተከትሎ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ከ239 ሰዎች በላይ መገደላቸውን መንግስት መግለጹ ይታወሳል፡፡
በወቅቱ አል ዐይን አማርኛ ያነጋገራቸው የጉዳቱ ሰለባዎች በ “ብሄርና በሃይማኖት” ማንነታቸው ጥቃት እንደደረሰባቸው ቢገልጹም የኦሮሚያ ክልል ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት አልደረሰም ሲል አስተባሏል፡፡
ፓርቲው ከዚህ በተጨማሪም ሰሞኑን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት የሆኑት ሽመልስ አብዲሳ ከሰባት ወር በፊት ተናግረውት ነበር የተባለውና በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው ንግግር ተችቷል፡፡
የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ንግግሩ በይዘት ትክክል ያልሆነ፣ የግለስብ አቋም እንደሆነና በዝርዝር እንደሚገመገምም ገልጿል፡፡
በባህርዳር ሲካሄድ የነበረው ስብስባ ስኬታማ መሆኑን የገለጹት የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አገኘሁ ተሻገር ”ፓርቲው በ12ኛው የአዴፓ ጉባኤ የተያዙ የአማራ ህዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ” እየሰራ መሆኑንና “በአማራ ክልል አመራሮች ዙሪያ መከፋፈል” አለመኖሩንም አብራርዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ባህርዳር በተካሄደው የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ስብሰባ ላይ ተገኝተዋል፡፡