ከ25 ዓመት በፊት ደብዛው የጠፋው ሰው በጎረቤታቸው ቤት ታግቶ ተገኘ
ግለሰቡ ከታገተበት ሆኖ ቤተሰቦቹን ሲገቡ እና ሲወጡ ያይ ነበር ተብሏል
አጋቹ ድርጊቱን ለምን እንዳደረገው እስካሁን አልታወቀም
ከ25 ዓመት በፊት ደብዛው የጠፋው ሰው በጎረቤታቸው ቤት ታግቶ ተገኘ፡፡
ኦማር ቢን ኦምራን የተባለው ሰው ከ25 ዓመት በፊት ነበር ደብዛው የጠፋው፡፡
በሰሜናዊ አልጀሪያ የሚኖረው ይህ ወጣት ሀገሪቱ የእርስ በርስ ጦርነት በተቀሰቀሰበት 1998 ላይ በድንገት እንደጠፋባቸው ቤተሰቦቹ ተናግረው ነበር፡፡
ልጃቸው ጠፋባቸው እነዚህ ሰዎችን ፈልገው ሲያጡት በጦርነቱ ሳይገደል እንዳልቀረ መደምደሚያ ለይ ይደርሳሉ፡፡
የኦማር እናት ግን ልጃቸው ታግቶ ሳይወሰድ እንዳልቀረ ጥርጣሬ እንደነበራቸው በ2013 ህይወታቸው አልፏል ተብሏል፡፡
ይሁንና ይህ ልጃቸው ከ25 ዓመት በኋላ በጎረቤታቸው ቤት ውስጥ ታግቶ እንደሚኖር ተረጋግጧል፡፡
ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ቤቱን ሲፈትሽ ጎረምሳ የነበረው ኦማር የ45 ዓመት ጎልማሳ ሆኖ ከታገተበት ነጻ ወጥቷል ተብሏል፡፡
ግዙፍ “የሚስት አፋልጉኝ ማስታወቂያ” የለጠፉት አሜሪካዊ ውሃ አጣጬ ከወዴት አለሽ እያሉ ነው
አጋቹ ለምን ይህን የጎረቤታቸውን ልጅ ለዚህ ሁሉ ዓመታት በመሬት ውስጥ አግቶ እንዳቆየው እና ምን እንደሚፈልግ እስካሁን አልታወቀም፡፡
ታጋቹ ከጎረቤት ሆኖ አልፎ አልፎ ቤተሰቦቹ ሲወጡ ሲገቡ ያይ ነበር የተባለ ሲሆን እርዳታ እንዳይጠራ መናገር እንዳይችል ተደርጎ መታገቱን እና ከእገታው ከተለቀቀ በኋላም መናገር እንደማይችል የአልጀሪያ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡
ለዓመታት ታግቶ የቆየው ይህ አልጀሪያዊ የስነ ልቦና እና ሌሎች ህክምናዎችን እየተደረገለት ነው የተባለ ሲሆን ፖሊስ በአጋቹ ላይ ምርመራውን እንደቀጠለ ነው ተብሏል፡፡