አሜሪካ እና ብሪታንያ የቀይ ባህርን ደህንነት ለማስጠበቅ በሚል በሁቲ ታጣቂዎች ላይ ጥቃት መክፈታቸው ይታወሳል
አሜሪካ በሶማሊያ ወደብ ዘመቻ ላይ የነበሩ መርከበኞቿ እንደጠፉባት ገለጸች፡፡
አሜሪካ እና ብሪታንያ በትናንትናው ዕለት በየመን የሁቲ ታጣቂ ይዞታዎች ላይ ጥቃት ማድረሳቸው ይታወሳል፡፡
ሀገሪቱ እንዳሳወቀችው በሶማሊያ ባህር ላይ ዘመቻ በማድረግ ላይ የነበሩ ሁለት መርከበኞቿ እንደጠፉባት ገልጻለች፡፡
የአሜሪካ ወታደራዊ ተቋም የጠፉ ወታደሮችን የመፈለጉ ጥረት ከትናንትናው ዕለት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ነውም ተብሏል፡፡
ስለጠፉት ወታደሮች ማንነት እና ተያያዥ ተጨማሪ መረጃዎች ለጊዜው ይፋ እንደማይደረጉም ተቋሙ አስታውቋል፡፡
እስራኤል በጋዛ የጀመረችውን ጦርነት ካላቆመች በሚል በእስራኤል እና አጋሮቿ ላይ ጥቃት በማድረስ ላይ ያለው የየመኑ ሁቲ ታጣቂ ከሰሞኑ በአሜሪካ እና ብሪታንያ ጦር ጥቃት ተፈጽሞበታል፡፡
አሜሪካ እና የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ሉዓላዊነት እንዲከበር ጠየቁ
የአየር ድብደባው በሰንአ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ፣ በሆዴይዳ የሃውቲ ባህር ሃይል ጣቢያ እና በታይዝ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ መፈጸሙን ሬውተርስ የአይን እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል።
ከደርዘን በላይ ይሆናሉ የተባሉት ጥቃቶች በአውሮፕላን እና ከመርከቦች ላይ በተተኮሱ ሚሳኤሎች አማካኝነት የተፈጸሙ እንደሆኑ ተገልጿል።
ቱርክ፣ ኢራን እና ሳውዲ አረቢያ አሜሪካ እና ብሪታንያ የፈጸሙትን ጥቃት ያወገዙ ሲሆን ቀይ ባህር ወደተባባሰ ጉዳት እየገባ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው በየመን የተፈጸመውን ጥቃት ያወገዙ ሲሆን የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሊዮድ ኦስቲን ሆስፒታል ሆነው በላፕቶፓቸው የሚመሩት ዘመቻ ግቡን አይመታም ሲሉ ተችተዋል፡፡