ጎግል በአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ታሪክ ግዙፍ የተባለ ማሻሻያ ይፋ አደረገ
አዲሱ ማሻሻያ ከቤት ሆኖ ስራ መስራትን የሚያቀል አገልግሎት በውስጡ የያዘ ነው
የአንድሮይድ 12 መሻሻያ ከኮሮና ወረርሽኝ ወዲህ በተካሄድ የቴክኖሎጂ አልሚዎች ኮንፈረንስ ላይ ነው ይፋ የተደረገው
የአሜሪካው ጎግል ኩባንያ በአንድሮይድ 12 ኦፕሬቲንግ ሲሰተሙ ላይ ከፍተኛ ነው የተባለ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ።
ጎግል ይፋ ያደረገው ማሻሻያ በአንድሮይድ ታሪክ ግዙፉ የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ማሻሻያ መሆኑን ኩባንያው አስታውቋል።
የአንድሮይድ 12 የኦፕሬቲንግ ሲስተም መሻሻያ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄድ የቴክኖሎጂ አልሚዎች ኮንፈረንስ ላይ ይፋ ማድረጉም ታውቋል።
የአንድሮይድ 12 ማሻሻ ምን አዲስ ነግር በውስጡ ይዟል
- የካሜራ ጨምሮ ልሎች መተግበሪያ ስንከፍት የግል መረጃዎቻችንን ደህንነት የሚጠብቅ አዲስ አግልግሎት
የአንድሮይድ 12 የኦፕሬቲንግ ሲስተም አዲሱ ማሻሻያ ካሜራን ጨምሮ ሌሎች መተግበሪያዎችን በምንከፍትበት ጊዜ በስልካችን ላይ የያዝነው መረጃ ለሌሎች መረጃ መንታፊዎች እንዳይጋለጥ የሚያድርግ የደህንነት መጠበቂያ ወዲያው የሚከፈት ይሆናል።
- ከቤት ሆኖ ስራ መስራትን የሚያቀል አገልግሎት
ማሻሻያው በተለይም ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ስራን ከቤት ሆኖ መስራት ግድ በሆነበት በአሁኑ ጊዜ ይህን የሚያቀል አግግሎት ይዞ መምጣቱ ታውቋል።
ይህም የጎግል ዶክስ (Google Docs) እና ሌሎች ቡክማርኮችን በቀላሉ መጠቀም የሚያስችል ነው ተብሏል።
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ የሰዓት እና ልሎችም በአንድሮይድ 12 የኦፕሬቲንግ ሲስተም አዲሱ ማሻሻያ መካተታቸው ታውቋል።