አሜሪካ በቴክኖሎጂ ኩባንያዎቿ ላይ የሚጣሉ የዲጂታል ግብሮችን ተቃውማለች
ኬንያ በቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ላይ 1.5% ግብር ጣለች
በሀገሪቱ በኦንላይን ቢዝነስ ተሰማርተው በሀገሪቱ ንግድ ከሚያካሂዱ እና ትርፍ ከሚያገኙ የበይነ መረብ ኩባንያዎች የበለጠ ገቢ ለመሰብሰብ ኬንያ 1.5% የዲጂታል ግብር እንደምትጥል አስታወቀች፡፡
የሀገሪቱ የገንዘብ ሚኒስትር ኡኩር ያታኒ በአውሮፓውያኑ 2020/21 በጀት ዓመት የበጀት መግለጫ በሰጡበት ወቅት ስለ ዲጂታል ግብሩ መጣል መግለጻቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ግብሩ ከሀምሌ 1 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ኬንያ እንደ ጉግል ፣ ኔትፊሊክስ እና ፌስቡክ ባሉ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ላይ ግብር ከጣሉ ሀገራት ዝርዝር ዝርዝር ዉስጥ ትገኛለች፡፡
አሜሪካ ደግሞ በዲጂታል ኩባንያዎች ላይ የሚጣሉ ግብሮች የአሜሪካን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች “ያለአግባብ ኢላማ ያደረጉ ናቸው” በሚል ትቃወማለች ፡፡ በአሜሪካ ትላልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ላይ የግብር ጫና ለመጨመር አቅደዋል ባለቻቸው ዩናይትድ ኪንግደም ፣ የአውሮፓ ህብረት እና ህንድን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ላይ አሜሪካ ጥናት ባለፈው ሳምንት ጥናት ጀምራለቸ፡፡
ሀገራቱ የዲጂታል አገልግሎቶችን ግብር ከ 2 እስከ 15% ያደረሱ እንደሆኑ የተገለጸ ሲሆን ከአሜሪካ የበቀል እርምጃ ሊጠብቃቸው ይችላል ተብሏል፡፡
ኬንያን በተመለከተ ወደ አሜሪካ ከቀረጥ ነጻ በምታስገባቸው ሸቀጦች ላይ ተጽእኖ ሊያሳድርባት እንደሚችል ተሰግቷል፡፡