70 ሚሊዮን ዶላር የወጣበት የሪያድ ቦክስ ውድድር ሊጀመር ሰዓታት ቀርተውታል
ትውልደ ናይጀሪያዊው ጆሽዋ እና ካሜሩናዊው ንጋኑ በሪያድ ዛሬ ምሽት ይፋለማሉ
ብዙ የቦክስ ስፖርት ባለሙያዎች አሸናፊነቱን ለአንቶኒ ጆሽዋ ቢሰጡም ንጋኑ ሊያሸንፍ እንደሚችልም ተገምቷል
70 ሚሊዮን ዶላር የወጣበት የሪያድ ቦክስ ውድድር ሊጀመር ሰዓታት ቀርተውታል።
የቦክስ ውድድር በትንሽ ጊዜ ውስጥ ቢካሄድም በአንድ ጊዜ ሚሊዮኖን ዶላሮችን የሚያሸልም ስፖርት ነው።
በዛሬው ዕለትም በሳዉዲ አረቢያ መዲና ሪያድ ትውልደ ናይጀሪያዊው እና በዜግነት ብሪታንያ የሆነው አንቶኒ ጆሽዋ ከካሜሩናዊው ፍራንሲስ ንግኑ ይፋለማሉ።
ሳውዲ አረቢያ ይህንን ውድድር ያዘጋጀችው ስፖርትን ለማስፋፋት ባላት ፍላጎት እንደሆነ አስታውቃለች።
እንደ ፎርብስ መረጃ ከሆነ ሳውዲ አረቢያ አንቶኒ ጆሽዋ በዚህ ውድድር ላይ እንዲካፈል 50 ሚሊዮን ዶላር ስትከፍል ለፍራንሲስ ንጉማ ደግሞ 20 ሚሊዮን ዶላር ከፍላለች።
ምሽት አራት ሰዓት የሚካሄደው ይህን ውድድር በርካታ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በቀጥታ እንደሚያስተላልፉት አስቀድመው ተናግረዋል።
ውድድሩ በ10 ዙር እንደሚካሄድ ሲጠበቅ ሁለቱም ተፋላሚዎች ያላቸው የማሸነፍ ታሪክን መሰረት በማድረግ ውድድሩ በዝረራ የማለቅ እድሉ የጠበበ ነውም ተብሏል።
በዚህ ምክንያትም ውድድሩ እስከ መጨረሻው ዙሪ የመሄድ እድሉ ሰፊ እንደሆነ ተገልጿል።
የልጅነት አስተዳደጉ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዳለፈንየተገለጸው እና የ37 ዓመቱ ንጋኑ ያለው ጉልበት አደገኛ ቦክሰኛ አድርጎታል ተብሏል።
የሁለት ጊዜ ዓለም ቦክስ አሸናፊው አንቶኒ ጆሽዋ ከፍተኛ የማሸነፍ ግምት የተሰጠው ቢሆንም በንጋኑ ሊሸነፍ እንደሚችል በሪያዱ ውድድር ላይ መሳተፉም በቦክስ ታሪክ ያለውን የአሸናፊነት ታሪክ ሊጎዳበት ይችላል ሲሉ ባለሙያዎች ተናግረዋል።