የሁለቱ ቢሊየነሮች የቦክስ ፍልሚያ በኤክስ በቀጥታ እንደሚተላለፍ መስክ ገለጸ
በወቅቱ የትዊተር የህግ ወኪል ትሪድስ የትዊተርን አሰራር በመኮረጁ እከሳለሁ ሲል አስፈራርቶም ነበር
የኤክስ ባለቤት መስክ በትናንትናው እለት እንደተናገረው ለሚያደርገው የቦክስ ፍልሚያ የክብደት ማንሳት ልመምድ እያደረገ ነው
በቢሊየነሮቹ በኢለን መስክ እና በማርክ ዛከርበርግ መካከል ይደረጋል የተባለው የቦክስ ፍልሚያ በኤክስ ወይም ቀደም ሲል ትዊተር በሚባለው ላይ በቀጥታ እንደሚተላለፍ መስክ ገልጿል።
የኤክስ ባለቤት መስክ በትናንትናው እለት እንደተናገረው ለሚያደርገው የቦክስ ፍልሚያ የክብደት ማንሳት ልመምድ እያደረገ ነው።
ነገሮግን መስክ በፍልሚያ ዙሪያ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተጥቧል።
የሜታ ባለቤቱ ዛከርበርግ እና መስክ በፍርግርግ አጥር ውስጥ ለመፋለም ዝግጁ መሆናቸውን መናገራቸው ይታወሳል።
ሀለቱ ቢሊየነሮች የመጋጠም እድላቸው ከፍ ያላው ዛከርበርግ ባለፈው ወር ትዊተርን የሚወዳደር ትሪድስ የተሰኘ መተግበሪያ ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው።
መስክ በፈረንጆቹ ጥቅምት 2022 ትዊተርን ከገዛ በኋላ በቴክኒክ ጉዳዮች እና በጥላቻ ንግግር ዙሪያ ያሳለፋቸው ፖሊሲዎች በተጠቃሚዎች ዘንድ ግራመጋባትን ፈጥረው ነበር።
ሜታ ትሪድስን ሲያስተዋውቅ ጥቂቶች የትዊተር ሚና የሚቀንስ መስሏቸው ነበር፤ መተግበሪያውም እንደተጀመረ ጥሩ ስኬት ላይ ደርሶ ነበር።
በወቅቱ የትዊተር የህግ ወኪል ትሪድስ የትዊተርን አሰራር በመኮረጁ እከሳለሁ ሲል አስፈራርቶም ነበር።
መስክም ይሁን ዛከርበርግ ለመፋለም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሲኤንኤን አለማረጣጠጡን ዘግቧል።