የደቡብ አፍሪካውን አፖርታይድ የሰነደው የፎቶ ጋዜጠኛ አረፈ
ከአስር አመት በኋላ በሰዌቶ የነበረውን የተማሪዎች አመጽ በመሸፈን አለምአቀፍ ሽልማትን አሸንፋል
ሙጉባኔ በ1990 ከእስር የተፈቱት የኔልሰን ማንዴላ ፎቶግራፈር ሆኖ ሰርቷል
የደቡብ አፍሪካውን አፖርታይድ የሰነደው የፎቶ ጋዜጠኛ አረፈ።
በደቡብ አፍሪካ የተካሄደውን የአፖርታይድ ስርአት በፎቶ የሰነደው የፎቶ ጋዜጠኛ ፒተር ማጉባኔ በ91 አመቱ አረፈ።
በአፖርታይድ ስርአት ወቅት የጥቁሮች የእለት ከእለት ህይወት ምን ይመስል እንደነበር በፎቶ የሰነደው የፎቶ ጋዜጠኛ ፒተር ሙጉባኔ ህይወቱ ማለፉን ሮይተርስ ዘግቧል።
ዱሩም የተባለውን መጽሄት በ1955 የተቀላቀለው ሙጉባኔ ጨቋኝ የነበረውን ስርአት በማሳየት እውቅና ካገኙ ጥቂት ጥቁር የፎቶግራፍ ጋዜጠኞች አንዱ ነው።
መጽሄቱን ከተቀላቀለ ከአንድ አመት በኋላ ሀብታሞች በሚኖሩበት የጆሀንስበርግ ዳርቻ አንዲት ነጭ ልጅ "ለአውሮፖውያን ብቻ" ተብሎ በተጻፈበት አግዳሚ ወንበር ላይ ቁጭ ብላ ሌላ ጥቁር ስራተኛ ከደርባዋ ቁጭ ብላ ጸጉሯን ስታቀጥር የሚያሳየው ፎቶው ከፍተኛ እውቅና አስገኝቶለታል።
የጸረ-አፖርታይድ ትግሉ እየተፋፋመ በመጣበት በ1960ዎቹ ደግሞ የኔልሰን ማንዴላን እስር እና የአሁኑን ገዥ ፖርቲ 'አፍሪካን ኮንግረስ' መታገድን ሸፍኗል።
ከአስር አመት በኋላ በሰዌቶ የነበረውን የተማሪዎች አመጽ በመሸፈን አለምአቀፍ ሽልማትን አሸንፋል።
ሙጉባኔ በዚህ ስራው በተደጋጋሚ ዛቻ፣ ጥቃት እና የ586 ቀናት እስራት አጋጥሞታል።
ነገርግን ይህ ስራውን እንዲያቆም አላደረገውም፣ በ1990 ከእስር የተፈቱት የኔልሰን ማንዴላ ፎቶግራፈር ሆኖ ተቀጥሮ ሰርቷል።