ፓሀድ አፖርታይድ ከተወገደ በኋላ ሁለተኛ በሆኑት ታቦ ምቤኪ የስልጣን ዘመን በፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በሚኒስትርነት ተሾመው ነበር
በውጭ ሀገር ኮብልለው አስርት አመታትን ያሳለፉት የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ጸረ-አፖርታይድ ታጋይ ኢሶፕ ፓሀድ በ84 አመታቸው አረፉ።
ፓሀድ ባደረባቸው የካንሰር ህመም ምክንያት በትናንትናው እለት ህይወታቸው ማለፉን ሮይተርስ ዘግቧል
ፖሀድ ደቡብ አፍሪካን ሲመሩ በነበሩት አናሳ ነጮች ሀገሪቱን በግድ እንዲለቁ ከተገደዱት በርካታ የመብት ተሟጋቾች ውስጥ አንዱ ነበሩ።
ባለስለጣናት ፓሀድን በፈረንጆቹ 1962 ሀገወጥ አድማ አስተባብረሀል በሚል አስረዋቸው ነበር፤ ቆይቶም ከደቡብ አፍሪካ እንዲባረሩ ተደርገው ነበር።
ፓሀድ አፖርታይድ ከተወገደ በኋላ ሁለተኛ በሆኑት ታቦ ምቤኪ የስልጣን ዘመን በፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በሚኒስትርነት ተሾመው ነበር።
ፖሃድ የህንድ ዝርያ ያላቸዎ ደቡብ አፍሪካዊ ናቸው።
ፕረዝደንት ሲሪል ራማፎዛ ለፓሀድ ብሔራዊ የቀብር ስነ ስርአት እንዲደረግ ባወጁበት መግለጫቸው በቀድሞ ታጋዩ ሞት ማዘናቸውን ገልጸዋል።
ፖሀድ ኢፍትሃዊነት የሚታገል አሳቢ እና ስትራቴጂስት ነበር ብለዋል ፕሬዝደንቱ።