ፖለቲካ
ግብጻዊው አቡል ጌት የአረብ ሊግ ዋና ጸሐፊ ሆነው በድጋሚ ተመረጡ
የአቡል ጌይት በድጋሚ መመረጥ “የሊጉ ዋና ጸሃፊ ምንጊዜም ከወደ ግብጽ ነው” የሚለውን ዘልማድ ያስቀጠለ ነው፡፡
የ78 ዓመቱ አዛውንት ለቀጣይ 5 ዓመታት ቀጣናዊውን ተቋም በዋና ጸሃፊነት የሚመሩ ይሆናል ተብሏል
የአረብ ሊግ ዋና ጸሐፊ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት የቀድሞው የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ አቡል ጌት የሊጉ ዋና ጸሃፊ ሆነው ዳግም ተመረጡ፡፡
አቡል ጌት ቀጣናዊውን ተቋም እንዲመሩ የተመረጡት የሊጉ አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በግብጽ ባደረጉት ስብሰባ ነው፡፡
በዚህም በፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ አቅራቢነት እጩ ሆነው የቀረቡት የ78 አመቱ አዛውንት ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ሊጉን የሚመሩ ይሆናል፡፡
አዛውንቱ አንጋፋውን ዲፕሎማት እና የዓለም አቀፍ ህግ ባለሙያውን ነቢል ኤል አረቢን ተክተው ነበር ከ5 ዓመታት በፊት ሊጉን መምራት የጀመሩት፡፡
ኤል አረቢ የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ነበሩ፡፡
የአቡል ጌይት በድጋሚ መመረጥ “የሊጉ ዋና ጸሃፊ ምንጊዜም ከወደ ግብጽ ነው” የሚለውን ዘልማድ ያስቀጠለ ነው፡፡
እ.ኤ.አ በ1945 የተመሰረተው ሊጉ ሃገራትን ለጦርነት ለጋበዙ ችግሮች እልባት ለመስጠት ባለመቻሉ ይወቀሳል፡፡