የኳታር ኤሚር ፎቶ ብቻ ተነስተው ከልእካቸው ጋር ጉባዔውን አቋርጠው መውጣታቸው ተነግሯል
ብዙ ክስተት የተስተናገደበት 32ኛው የአረብ ሊግ ጉባዔ በዛሬው እለት በሳዑዲ አረቢያዋ ጄዳህ ተካሂዷል።
በጉባዔው ላይ የሳዑዲ አረቢያ ልኡል አልጋ ወራሽ እና ጠቅላይ ሚኒስትር መሃመድ ቢን ሰልማንን ጨምሮ የተለያዩ የአረብ ሀገራት መሪች ተገኝተዋል።
ለ12 ዓመታ ከአረብ ሊግ ተገላ የቆየችው ሶሪያ በፕሬዝዳንተቷ በሽር አል አሳድ ተወክላ በጉባዔው ላይ ተሳትፋለች።
ከሩሲያ ጋር ጦርነት ውስጥ ያለችው ዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪም በጉባዔው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ተገኝው ንግግር ማድረጋቸው ተነግሯል።
የኳታሩ ኤሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ በጉባዔው ላይ ልኡካቸውን ይዘው የተገኙ ቢሆንም፤ የቡድን ፎቶግራፍ ላይ ብቻ ተነስተው መመለሳቸው ተነግሯል።
ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ በጉባዔው ላይ ሀገራቸውን በመወከል ምንመ ንግግ ሳያደርጉ ልኡካቸውን ይዘው መመለሳቸውም ታውቋል።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪም በሳዑዲ አረቢያው የአረብ ሊግ ጉባዔ ላይ ተገኝተው ንግግር ማድረጋቸው ነው የተገለፀው።
በጉባዔው ላይ የሳዑዲ አረቢያ ልኡል አልጋ ወራሽ እና ጠቅላይ ሚኒስትር መሃመድ ቢን ሰልማን የአረብ ሊግ ፕሬዝዳንት ስፍራን ከአልጄሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር አይመን ቢን አብዱል ራህማ እጅ ተረክበዋል።
በጉባዔው ላይ የአረብ ሀገራት መሪዎች በጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ የተወያዩ ሲሆን፤ በሱዳን እየተካሄደ ያለው ጦርነት እንዲሁም የየመን እና የፊልስጤም ጉዳይ የውይይታቸው አጀንዳ ነበር ተብሏል።