ኢሚሬትስ ከ7ወር በፊት ያስወነጨፈቻት መንኮራኩር ነገ ማርስ ላይ ታርፋለች ተብሎ ይጠበቃል
ለአረቡ አለም የመጀመሪያ የሆነችው መንኮራኩር ማርስ ላይ ልታርፍ ነው
መንኮራኩሯን ለማስወንጨፍ 200 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጭ መደረጉን ዩኤኢ ማስታወቋ ይታወሳል
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ(ዩኤኢ) ያስወነጨፈቻት “ፕሮብ ኦፍሆፕ” የተሰኘችው መንኮራኩር ፍጥነቷን ቀንሷ በነገው እለት ማርስ ላይ ታርፋለች፤ይህም የዩኤኢን እያደገ የመጣውን የስፔስ ሳይንስና እውቀት ማእከነት ያጠናክራል ተብሏል፡፡
መንኮራኩሯ የተወነጨፈችው ተንጋሽማ ከተባለው የጃፓን የጠፈር ማእከል ሲሆን ወደ ጠፈር ደርሳ መረጃ ለመላክ የ7 ወር ጊዜ እንደሚፈጅባት ከሰባት ወር በፊት ስትወነጨፍ ተገልጾ ነበር፡፡ ወደ ጠፈር የማስወንጨፍ ስራው ባለፈው ሳምንት ሊካሄድ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም የአየር ጸባዩ ጥሩ ባለመሆኑ ሁለት ጊዜ ሊራዘም መቻሉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
መንኮራኩሯ ከተወነጨፈች አንድ ሰአት በኋላ መሬት ካለው የራዲዮ ኮሙኒኬሽን ጋር ግንኙነት መፍጠር ችላ ነበር፡፡
“ፕሮብ ኦፍሆፕ” ሞተሯን በመጠቀም ከፍተኛውን ፍጥነቷን በግማሽ ሰአት ውስጥ ትቀንሳለች፤ፍጥነት መቀነሷ ከተሳካ ኤርክራፍቷም ፍጥነት ስለሚቀነስ በጨረቃ ስበት ተስባ ወደ ማርስ ኦርቢት እንደምትገባ ይጠበቃል፡፡
መንኮራኩሯ ማርስ ከደረሰች በኋላ ለሁለት አመት ያህል በመቆየት ማርስን ታጠናለች፡፡ከዚህ በተጨማሪም መንኮራኩሯ የውሃ ትነትን መያዝ የሚችለው ወፍራም ከባቢ አየር እንዴት ጠፍቶ፤ ቀስ እያለ ወደ ደመናና ደርቅ ከባቢ ተቀየረ ሚለውንም ታጠናለች፡፡
የዩኤኢ ማርስን የማሰስ ፕሮጀክት ወይም ፕሮብ ኦፍ ሆፕ ከአረቡ አለም የመጀመሪያ ሲሆን ከ46 በላይ የሚሆኑ የአረብና እስላሚክ ሀገራት የአረብ ሳይንስና ጥናት መኖሩን ለማስመዝገብ የሚያነቃቃ ትልቅ ፕሪጀክት ነው ተብሏል፡፡
ፕሮብ ኦፍ ሆፕ በትክክል በማርስ ኦርቢት ላይ የምትርፍ ከሆነ ዩኤኢ ይህን ስኬት ከስመዘገቡ ቀዳሚ የአለም ሀገራት አምስተኛ ትሆናለች፡፡
መንኮራኩሯ በናቻፋችበት ወቅት የዩኤኢ የሳይንስ ሚኒስትር ሳራህ አሚሪ ለማስወንጨፍ 200 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጭ መደረጉን ተናግረው ነበር፡፡ የመንኮራኩሯ መወንጨፍ የማሪታንን አየርጸባይና፣ የእለታዊና የወቅታ ለውጦችን ሙሉ መረጃ መሰብሰብ አላማው መሆኑ ተዘግቧል፡፡
ኤምሬትስ መንኮራኩር ለመላክ አስባ የነበረው ከ7 አመታት በፊት ነበር፡፡ ዩኤኢ 9.4 ሚሊዮን ህዝብ ያላት በመካከለኛው ምስራቅ የምትገኝ ሀገር ስትሆን ከዚህም ውስጥ አብዛኞቹ የውጭ ሀገር ዜጎች ናቸው፡፡