“የዩኤኢ እና የእስራኤል የሰላም ስምምነት የአረቦችን አዎንታዊ ስትራቴጂካዊ ለውጥ የሚያሳይ ነው”-አንዋር ጋርጋሽ
የዩኤኢ እና የእስራኤል የሰላም ስምምነት በቀጣናው ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተንታኞች ይገልጻሉ
በሁለቱ ሀገራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ገና ዉይይቶች እንደሚቀሩ የዩኤኢ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ገልጸዋል
በሁለቱ ሀገራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ገና ዉይይቶች እንደሚቀሩ የዩኤኢ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ገልጸዋል
“የዩኤኢ እና የእስራኤል የሰላም ስምምነት የአረቦችን አዎንታዊ ስትራቴጂካዊ ለውጥ የሚያሳይ ነው”-አንዋር ጋርጋሽ
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የውጭ ጉዳይ እና ዐለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አንዋር ጋርጋሽ እንደገለፁት በ ዩኤኢ እና እስራኤል መካከል የተረሰው የሰላም ስምምነት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነቶች ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ነው፡፡ ለሁለቱም ሀገራት አስፈላጊ በሆኑ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ምክንያታዊ እና ተጨባጭ ውይይትቶች ገና እንደሚቀሩም ገልጸዋል፡፡
ይህን የስትራቴጂ ለውጥ እና የተደረሰውን ስምምነት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማድነቁን እና በደስታ መቀበሉን አንዋር ጋርጋሽ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው እንዳሉት “የዚህ ሽግግር ተሸናፊዎች የፖለቲካ ጉዳይ ነጋዴዎችና ደላላዎች ናቸው”፡፡
በሌላ በኩል ፣ ከዚህ ስምምነት ጋር በተያያዘ “መብቶች እየተከበሩ ይቀጥላሉ እንጂ የሚጣስ መብት የለም” ያሉት አንዋር ጋርጋሽ ይልቁንም ስምምነቱ “ለእንደዚህ አይነት ለውጦች ዕድሎችን የሚያጎለብት ነው” ብለዋል፡፡
“ይህ ቆራጥ የሆነ የኤሚሬቶች ዉሳኔ እረፍት ያጣውን ዉሃ እንዲሰክን አድርጎታል” ሲሉም ገልጸዋል፡፡ ነባራዊዉን ሁኔታ መለወጥ ግድ መሆኑንም ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታው አንዋር ጋርጋሽ ስምምነቱ በአረቡ ዓለም ዉስጥ ተለምደው የነበሩ በጎ ያልሆኑና ህመም የሚፈጥሩ አሉታዊ ቃላትን የሚቀይር መሆኑን በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ አብራርተዋል፡፡
ዩኤኢ እና እስራኤል የደረሱት የሰላም ስምምነት በዓለም አቀፍ መንግስታት እና ህዝቦች ከፍተኛ አድናቆት የተረው ሲሆን ስምምነቱን ከተቃወሙ ጥቂት ሀገራት መካከል የሆነችው ኢራን በዩኤኢ ላይ መዛቷ ይታወቃል፡፡ ይህን ዛቻ በመቃወም የዩኤኢ ዉጭ ጉዳይ እና ዐለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር በአቡዳቢ የሚገኘውን የኢራን ኤምባሲ ወኪል አምባሳደር ጠርቶ አነጋግሯል፡፡ ሚኒስቴሩ ኢራን ከድርጊቷ እንድትታቀብ እና በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት የዩኤኢን ሉዓላዊ መብት እንድታከብር አሳስቧል፡፡ የባህረ ሰላጤው ሀገራት ትብብር ምክር ቤትም በተመሳሳይ የኢራንን ዛቻ በመቃወም ም/ቤቱ አባል ሀገራትን በጋራ መከላከል በሚለው መርሁ መሰረት ከዩኤኢ ጎን እንደሚቆም ገልጿል፡፡