“የአረፋ ኹጥባ” አማርኛን ጨምሮ በ20 ቋንቋዎች እንደሚተረጎም ተገለጸ
የ1445ኛው የሃጅ ስነ ስርዓት ዛሬ በይፋ ተጀምሯል
የአረፋ ኹጥባ ብዙ ተናጋሪ ባላቸው 20 ቋንቋዎች ተተርጉሞ ለ1 ቢሊየን ሰዎች እንዲደርስ ይደረጋል ተብሏል
የ1445ኛው የሃጅ ስነ ስርዓት ዛሬው እለት በሳዑዲ አረቢያ መካ በይፋ ተጀምሯል።
በዳሁል ሂጃህ ወር ከሚከናወነው የሃጅ ስነ ስርዓት ውስጥ በ9ኛው ቀን የሚፈጸመው “የአረፋ” ስነ ስርዓት እንዱ ነው።
ታዲያ ይህ “የአረፋ ኹጥባ” ስነ ስርዓት ዘንድሮ በመላው አለም ብዙ ተናጋሪ ባላቸው 20 ቋንቋዎች እንደሚተረጎም የሁለቱ ቁዱሳን መስጊዶች አስተዳደር ሃራማይን ሸሪፈይን አስታውቋል።
በአረብኛ ቋንቋ የሚከነወነው የአረፋ ኹጥባ በመላው አለም ብዙ ተናጋሪ ባላቸው 20 ቋንቋዎች በመቶርገምም በዓለም ዙሪያ ለ1 ቢሊየን ሰዎች እንዲደርስ እንደሚደረግም ተገልጿል።
የአረፋ ኹጥባ ተተርጎሙ ከሚተላለፍባቸው ቋንቋዎች መካከል አማርኛ ቋንቋ እንዱ እንደሆነም ተነግሯል።
በተጨማሪም የአረፋ ኹጥባ በእንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይና፣ ማላይ፣ ኡርዱ፣ ፋርሲ፣ ቻይኒዝ (ማናዳሪን)፣ ቱርኪሽ፣ እና የሩሲያኛ ቋንቋዎች እንደሚተረጎም ታውቋል።
እንዲሁም፣ ሃውሳ፣ ቤንጋሊ፣ ስዊድሽ፣ ስፓኒሽ፣ ሳዋሂሊ፣ ጣሊያንኛ፣ ፖርጉጋልኛ፣ ቦስኒያን፣ ማላያላም፣ ፍሊፒኖ እና ጀርመንኛ ቋንቋዎችን ይተረጎማል ነው የተባለው።
ከ7 ዓመት በፊት የተጀመረውና በአረብኛ ቋንቋ የሚከነወነው የአረፋ ኹጥባ በመላው አለም ብዙ ተናጋሪ ባላቸው ቋንቋዎች ተተርጉሙ እንዲተላለፍ ሲደረግ ይፍ ለሰባተኛ ጊዜ እንደሆነም ነው የተገለጸው።
የ1445ኛው የሃጅ ስነ ስርዓት ዛሬው እለት በሳዑዲ አረቢያ መካ በይፋ ተጀምሯል። ዛሬ ምሽት ላይ ሀጃጆች ወደ ሚና ጉዞ ይጀምራሉ ተብሏል።
አመታዊውን የሀጅ የጸሎት ስነስርአት ለመታደም ከ1.8 ሚሊዮን በላይ ሀጃጆች መካ ከትመዋል። በተለያዩ የአለም ሀገራት የሚገኙ ሙስሊሞች የሚታደሙት አመታዊ ስነስርአት በሀይማኖቱ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ነው።
እስልምና ከሚያዛቸው 5ቱ መሰረታዊ ሀይማኖታዊ ግዴታዎች መካከል አንዱ እንደሆነም ይነገራል።