በአረብኛ ቋንቋ የሚከነወነው የአረፋ ኹጥባ በመላው አለም ብዙ ተናጋሪ ባላቸው 20 ቋንቋዎች ይተረጎማል
በተሳታፊዎች ብዛት በታሪክ ትልቁ የተባለው የ1444ኛው የሃጅ ስነ ስርዓት ዛሬው እለት በሳዑዲ አረቢያ መካ በይፋ ተጀምሯል።
በዳሁል ሂጃህ ወር ከሚከናወነው የሃጅ ስነ ስርዓት ውስጥ በ9ኛው ቀን የሚፈጸመው “የአረፋ” ስነ ስርዓት እንዱ ነው።
ታዲያ ይህ “የአረፋ ኹጥባ” ስነ ስርዓት ዘንድሮ በመላው አለም ብዙ ተናጋሪ ባላቸው 20 ቋንቋዎች እንደሚተረጎም የሁለቱ ቁዱሳን መስጊዶች አስተዳደር ሃራማይን ሸሪፈይን አስታውቋል።
የአረፋ ኹጥባ ተተርጎሙ ከሚተላለፍባቸው ቋንቋዎች መካከል አማርኛ ቋንቋ እንዱ እንደሆነም ተነግሯል።
በተጨማሪም የአረፋ ኹጥባ በእንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይና፣ ማላይ፣ ኡርዱ፣ ፋርሲ፣ ቻይኒዝ (ማናዳሪን)፣ ቱርኪሽ፣ እና የሩሲያኛ ቋንቋዎች እንደሚተረጎም ታውቋል።
እንዲሁም፣ ሃውሳ፣ ቤንጋሊ፣ ስዊድሽ፣ ስፓኒሽ፣ ሳዋሂሊ፣ ጣሊያንኛ፣ ፖርጉጋልኛ፣ ቦስኒያን፣ ማላያላም፣ ፍሊፒኖ እና ጀርመንኛ ቋንቋዎችን ይተረጎማል ነው የተባለው።
የ1444ኛው የሃጅ ስነ ስርዓት ዛሬው እለት በሳዑዲ አረቢያ መካ በይፋ ተጀምሯል። ዛሬ ምሽት ላይ ሀጃጆች ወደ ሚና ጉዞ ይጀምራሉ ተብሏል።
በዛሬው እለት የተጀመረው የዘንድሮ የሃጅ ስነ ስርዓት 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ሃጃጆች እንደሚሳተፉበት የሚጠበቅ ሲሆን፤ በተሳታፊዎች ብዛትም ክብረወሰን ሆኖ ሊመዘገብ ይችላል ተብሏል።