የመናውያን የሃጅ ተጓዦች
የሰንአ አውሮፕላን ማረፊያ ከ9 አመት በኋላ ለሲቪል መንገደኞች ተከፍቷል
የየመን አየርመንገድ የሃጅ ተጓዦችን በየቀኑ አራት በረራ በማድረግ ወደ ጂዳ ያደርሳል ተብሏል
የመናውያን የሃጅ ተጓዦች ከ9 አመታት በኋላ ትናንት ከሰንአ በአውሮፕላን ወደ ሳኡዲ አረቢያ አቅንተዋል።
የየመን አየርመንገድ በሃጅ ወቅት በቀን አራት ጊዜ ወደ ጂዳ ለመብረር ከሪያድ ጋር መስማማቱም ታውቋል።
በኢራን የሚደገፉት የሃውቲ ታጣቂዎች ሰንአን በቁጥጥር ስር አውለው አብድራቡ ማንሱር ሃዲን ከስልጣን ሲያነሱ፥ ሳኡዲ ወዳጆቿን አስተባብራ ወደ የመን መዝለቋ ይታወሳል።
ጥምር ጦሩ የየመንን የአየር ክልል ተቆጣጥሮ የነበረ ሲሆን፥ ሪያድ እና ቴህራንም ሰንአን የእጅ አዙር መፋለሚያ አድርገዋት ቆይተዋል።
ሳኡዲ እና ኢራን በቻይና አደራዳሪነት ባለፈው መጋቢት ወር ቅራኔያቸውን ለመፍታት ከተስማሙ በኋላ ግን በየመንም ሆነ በሌሎች የቀጠናው ሀገራት ያሉ ውጥረቶች እየረገቡ ይገኛሉ።
የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic