አፍሪካ ለማይቀርላት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ትኩረት ልትሰጥ እንደሚገባ ተጠቆመ
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በዓለም ገበያ ውስጥ ያለው ድርሻ ከ350 ቢሊየን ዶላር በላይ ደርሷል ተብሏልአ
የፓን አፍሪካ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጉባኤ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ያገኛል
ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጉባኤን በአዲስ አበባ በማስተናገድ ላይ ስትሆን በመድረኩ ላይ የአፍሪካ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ምሁራን፣ በዚሁ ሙያ የተሰማሩ ኩባንያዎች እና የተለያዩ ተጋባዥ ሀገራት በመሳተፍ ላይ ናቸው።
በአዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም በመካሄድ ላይ ያለው ይህ ጉባኤ ዋና ትኩረቱን በአፍሪካ አርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ ላይ አድርጓል።
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ተጠባባቂ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ፔድሮ በጉባኤው ላይ እንዳሉት ዓለም በአርቲፊሺያል እንተለጀንስ ታግዞ ምርታማነቱን እያሳደጉ መሆኑን ተናግረዋል።
አርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ በምዕራባዊያን እና ሩቅ መስራቅ ሀገራት ላይ በሰፊው እየተተገበረ መሆኑን የተናገሩት ዋና ጸሃፊው አፍሪካ ግን ገና በሙከራ ላይ እንደሆነች ጠቁመዋል።
ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ፣ ናይጀሪያ እና ጋና በአንጻራዊነት አርቲፊሺያል ኢንተለጀንስን ከመጠቀም አንጻር የተሸሉ ቢባሉም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያም ዘርፉን ለማሳደግ የጀመረቻቸውን ጥረቶች አድንቀዋል።
በዚህ መድረክ ላይ የሀገራቸውን ልምድ ለአፍሪካ ያካፈሉት የተባበሩት አረብ ኢምሬት የሳይበር ደህንነት ዳይሬክተር መሀመድ አል ኩዌቲ (ዶ/ር) በበኩላቸው ሀገራቸው አርቲፊሺያል ኢንተለጀንስን በስፋት እየሰራችበት እና ውጤታማ መሆኗን አክለዋል።
አረብ ኢምሬት በተለይም በኢንዱስትሪዎች፣ በጤና፣ በደህንነት እና በግብርና ዘርፎች አርቲፊሺያል ኢንተለጀንስን በመጠቀም የኢንዱስትሪዎቿን እና ተቋማቶቿን ውጤታማነት አሳድጋለች የሚሉት ዳይሬክተሩ ሀገራቸው ለአፍሪካ ልምዷን ለማካፈል እንደምትፈለግም ተናግረዋል፡፡
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በበኩላቸው ሳይንስ የሰው ልጆች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ዋነኛ መሠረት ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ኢትዮጵያ ከአርቲፊሺል ኢንተለጀንስ ለመጠቀም የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ማዘጋጀቷን እንዲሁም አስፈጻሚ ተቋማትን መስርታ ወደ ተግባር መግባቷንም አክለዋል፡፡
የአርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ አምራች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ከቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰር ያልተቋረጠ ምርት እና አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ የሚያስችል ስርዓት ነው፡፡
አትላንቲክ ካውንስል የተሰኘው ዓለም አቀፍ የጥናት ተቋም በ2021 ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት አርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ዓመታዊ የዓለም ገበያ ድርሻ 350 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።
ይህ ዘርፍ በተለይም የሰዎችን ንኪኪ በመቀነስ ለምርት መጨመር፣ የጊዜ አጠቃቀምን ለማሻሻል፣ ብልሹ አሰራሮችን ለማስወገድ እና ሌሎች ችግሮችን ለማስወገድ እንደሚጠቅም ይገለጻል።