የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከልን በጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ተመርቆ ተከፈተ
ማዕከሉ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀሳብ አመንጪነት በ2012 ዓ.ም የተቋቋመ ነው ተብሏል
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ምንድን ነው?
የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከልን በጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ተመርቆ ተከፈተ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከልን ዛሬ መርቀው ከፍተዋል።
ኢዜአ እንደዘገበው የተመረቀው ማዕከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሀሳብ አመንጪነት በ2012 ዓ.ም የተቋቋመ ነው።
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ) ማሽኖችን በመጠቀም ሰው ሰራሽ የሆነ የማሰብ ክህሎትን ለተለያዩ የስራ መስኮች የመጠቀም ቴክኖሎጂ ነው።
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ) ፣ አንዳንድ ጊዜ የማሽን ኢንተለጀንስ (የማሽን ማሰብ /የማሽን መረዳት/የማሽን የፈጠራ አቅም…) ተብሎም የሚጠራው በሰውና በእንስሳት ከሚታየው የተፈጥሮ የማሰብ ችሎታ በተለየ በማሽኖች ሀሳብ የተለያዩ ተግባራትን የመተግበር ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ሰው ሰራሽ ማሽኖች አካባቢያቸውን በመረዳት ትክክለኛውን እርምጃ በመውሰድ ለታለሙለት ተግባር አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ነው፡፡
በኢትዮጵያም የተቋቋመው ማዕከሉ ለግብርና፣ የትምህርት፣ ጤና እንዲሁም ለህብረተሰብ ጥበቃና ደህንነት አገልግሎቶች አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ለመጠቀም ታቅዶ የተከፈተ መሆኑ ተገልጿል።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆነውም አሁን ላይ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተደገፉ የጡት ካንሰርና የጭንቅላት እጢ መለየት በሚያስችሉ መተግበሪያዎችን እየሰራ ይገኛል።
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ በፍጥነት እያደገ የሚገኝ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ በተለይ የበለጸጉ ሀገራት ቴክኖሎጂውን ለበርካታ ዘርፎች በስፋት ይጠቀማሉ፡፡