ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአርቲስት አለማየሁ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል
አንጋፋው አርቲስት አለማየሁ እሸቴ በልብ ህመም ምክንያት ከዚህ አለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል፡፡
አርቲስቱ በትናንትናው እለት ከስራ ወደ ቤቱ ከገባ በኋላ በቆየው የልብ ህመም ተነስቶበት ለህክምና ሆስፒታል ከሄደ በኋላ በድንገት ህይወቱ ማለፉን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
አርቲስት አለማየሁ "ተማር ልጄ" በሚለውና ሌሎች አድናቆት ያተፈፉ ሙዚቃዎችን ተጫውቷል፡፡ አርቲስቱ ሙዚቃን የጀመረው በ1955ዓ.ም በፖሊስ ኦኬስትራ መሆኑን የኢቢሲ ዘገባ ጠቅሷል፡፡
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት ቴድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ የክብር ዶክትሬት ሰጠ
ለመጀመርያ ጊዜ በ1955 ዓ, ም በፖሊስ ሠራዊት ኦርኬስትራ በመቀጠር የሙዚቃ ሀሁን የጀመረው አንጋፋዉ ሙዚቀኛ አለማየሁ እሸቴ በወቅቱ በሚጫወታቸው የሙዚቃ ስራዎቹ ኤልቪስ ፕሪስሊ የሚል ቅፅል ተሰጥቶት ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአርቲስት አለማየሁ እሸቴ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡
“ሀገሩን አጥብቆ በመውደድና ለሀገሩ ከልብ በመሥራት ለብዙ ከያንያን አርአያ የሆነው ዓለማየሁ እሸቴ ማረፉን ሰምቼ እጅግ አዝኛለሁ። ሰሞኑን ወጣትና አንጋፋ ከያንያን ስለ ኢትዮጵያ ዘመኑን የዋጀ ሙዚቃ እንዲያወጡ ሲያስተባብር እንደነበር ዐውቃለሁ። ሥራዎቹ ኢትዮጵያን ከፍ እንዳደረጉ ይኖራሉ። ለኢትዮጵያ የሠራ ያርፋል እንጂ አይሞትም።” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገጻቸው አስፍረዋል፡፡