ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት ቴድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ የክብር ዶክትሬት ሰጠ
ቴዲ አፍሮ አቡጊዳ፣ ያስተሰርያል፣ ጥቁር ሰውና ኢትዮጵያ የተሰኙ የሙዚቃ አልበሞቹን ከአድናቂዎች ዘንድ አድርሷል
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 7 ሺህ 50 ተማሪዎቹን አስመርቋል
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት ቴድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ የክብር ዶክትሬት ሰጠ።
የጎንደር ዩኒቭርሲቲ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 7 ሺህ 50 ተማሪዎቹን በዛሬው እለት አስመርቋል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይም የውሃ መስኖን ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስተ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በዛሬው እለት በካሄደው የተማሪዎች ምርቃ ላይ ለአርቲስት ቴድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ የክብር ዶክትሬቱ ዲግሪ ሰጥቷል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሳለፍነው ሀሙስ ባካሄደው የሴኔት ስብሰባ ነው ለአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የክብር ዶክትሬት ለመስጠት የወሰነው።
ዩኒቨርሲቲው አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በሰብዓዊ፣ በማኅበራዊና በኪነ ጥበብ ዘርፉ እያበረከተ ላለው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነው የክብር ዶክተሬቱን ያበረከተለት።
በዚህም መሰረት አርቲስት ቴድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ በዛሬው እለት በጎንደር ተገኝቶ የክብር ዶክትሬት ዲግሪውን ተቀብሏል።
የግጥማ ዜማ ደራሲ ድምጻዊ አርቲስት ቴድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ አቡጊዳ፣ ያስተሰርያል፣ ጥቁር ሰው እና ኢትዮጵያ የተሰኙ የሙዚቃ አልበሞቹን ከአድናቂዎች ዘንድ አድርሷል።
እንዲሁም ለኃይሌ ገብረ ሥላሴ እና ለሌላኛው የኦሊምፒክ ጀግና ቀነኒሳ በቀለ በኦሊምፒክስ ካሸነፉ በኋላ ያወጣቸው ወቅታዊ ሙዚቃዎች፣ እንዲሁም ደግሞ በአባይ በሚል ያወጣው ነጠላ ዜማ ህዝቡ ዘንድ ተቀባይነትን አትርፈውለታል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀደምም ለአርቲስት አስቴር አወቀ የክብር ዶክትሬት መስጠቱ ይታወሳል።