
አርሜኒያን በበኩሏ አዘርባጃን የሰላም ድርድሩን ለማደናቀፍ እየሞከረች ነው ብላለች
የአዘርባጃን ፕሬዝደንት ኢልሃም አሊዬቭ ሀገራቸው ከአርሜኒያ ጋር በምታደርገው የሰላም ድርድር ላይ ፈረንሳይ እንድትሳተፍ እንደማይፈልጉ ገልጸዋል፡፡
በታህሳስ መጀመሪያ በብራስልስ ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና ከአውሮፓ ምክር ቤት ሃላፊ ቻርለስ ሚሼል ጋር ሊካሄድ የነበረውን የአራት መንገድ ስብሰባ አቋርጠዋል።
ፕሬዝደንቱ ማክሮን የአዘርባጃንን ዋና ከተማ ባኩን "አጥቅተዋል፤ ሰድበዋል" በሚል በሁለቱ ሀገራት መሀከል ሆነው ማደራደር እንደሌለባቸው ተናግረዋል፡፡
በሁለቱ የቀድሞ የሶቪየት ሀገራት መካከል በናጎርኖ-ካራባክ ግዛት ለአስርት ዓመታት የዘለቀው ውዝግብ በመስከርም ወር ዳግም አገርሽቷል፡፡
የውዝግብ አካባቢው በአለም አቀፍ ደረጃ የአዘርባጃን አካል እንደሆነ የታወቀ ቢሆንም፤ አካባቢው በጎሳ አርመናውያን ቁጥጥር ስር ነው።
በቅርቡ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን ባለፈው ወር በፕሮግ ሁለቱ ሀገራት የአውሮፓ ህብረት ተልዕኮ በድንበራቸው ላይ እንዲቋቋም ተስማምተዋል።
ነገር ግን ፕሬዝዳንት አሊዬቭ የአርሜኒያ ጠቅላይ ሚንስትር ኒኮል ፓሺንያን ፈረንሳይ አደራዳሪ መሆን አለባት በማለት ቀጣዩን የውይይት መድረክ ለማቃለል ሞክረዋል ሲሉ ከሰዋል።
"ማክሮን አዘርባጃን ላይ ጥቃት ሰንዝርዋለ፡፡ ያላደረግነውን ነገር አድርጋችኋል በሚል ከሰውናል" ሲሉ አሊዬቭ አሳውቀዋል፡፡
የፈረንሳዩ መሪ “ፀረ-አዘርባጃን አቋም” ይዘዋል፤ ባኩንም “ሰድበዋል” ብልዋል።
በዚህ አመለካከት ፈረንሳይ በአዘርባጃን እና በአርሜኒያ መካከል ያለው የሰላም ሂደት አካል መሆን እንደማትችል ግልጽ ነው ሲሉም ከድርድሩ እንድሚወጡ ተናግረዋል፡፡
የአርሜኒያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ማክሮን እና ሚሼል የተሳተፉበት የውይይት እንዲቀጥል እንደሚፈልግ ተናግሯል፡፡
ሮይተርስ የኢንተርፋክስ የዜና ወኪልን ጠቅሶ እንደዘገበው ቃል አቀባዩ ፕሬዝደንት ዬሬቫን የሰላም ድርድሩን ለማደናቀፍ እየሞከሩ ነው በማለት ክሱ ከእውነታው ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ሲሉ ተናግረዋል።