በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በአንድ ሆቴል ላይ በተከፈተ ተኩስ የሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ትናንት ህዳር 30 ቀን 2012 ዓ.ም. በአንድ ሆቴል ላይ በተከፈተ ተኩስ በትንሹ 7 ሰዎች ተገደሉ፡፡
የሶማሊያ ፖሊስ እንደ ገለጸዉ ተኩሱ የተከፈተው በሀገሪቱ የጸጥታ ሀይልና በታጣቂዉ አልሸባብ መካከል በሶማሊያ ወጣቶች ሊግ ሆቴል ዉስጥ ነዉ፡፡
በተደረገዉ የተኩስ ልዉዉጥም ሁለት የሀገሪቱ የጸጥታ ሀይል አባላትና ሶስት ንጹሀን ዜጎች ተገድለዋል፡፡
በተጨማሪም ሁለት የአልሸባብ ታጣቂዎች የሞቱ ሲሆን በትንሹ የ82 ሰዎችን ህይወት መታደጉን የገለጸዉ የሀገሪቱ ፖሊስ፣ የሟቾቹ ማንነት በዉል አልታወቀም ብሏል፡፡
ጥቃቱ የተጀመረዉ ማክሰኞ ከቀኑ 10 ሰዓት አከባቢ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት መኖርያ ቤት አከባቢ ጥበቃ ስራ ላይ በተሰማሩ የፀጥታ ሀይሎችና በአልሸባብ ታጣቂዎች መካከል መሆኑን በቢሲ ዘግቧል፡፡
የሶማሊያ ወጣቶች ሊግ ሆቴል በሀገሪቱ ባለስልጣናትና በባለሀብቶች ዘንድ ተወዳጅ ሆቴል ሲሆን ከዚ በፊትም ሶስት ጊዜ በአልሸባብ ጥቃት ደርሶበታል፡፡
በተመሳሳይ ነሐሴ 2016 በሆቴሉ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት 22 ሰዎች መሞታቸዉ ይታወሳል፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ