በኢትዮጵያ ለብዙ ዓመታት ተቀብራ የኖረች ጥንታዊ ከተማ ተገኘች
የቅሪተ አካል ተመራማሪዎች በኢትዮጵያ ጥንታዊ ከተማ ማግኘታቸውን አስታወቁ፡፡
ከተማዋ ለ1400 ዓመታት ተቀብራ ቆይታለች የተባለ ሲሆን ጥንታዊ ከተማዋ ለብዙ መቶ ዓመታት ምስራቅ አፍሪካን ከመቆጣጠርም ባለፈ እንደ ሮም ካሉ ሌሎች ታላላቅ ኃይሎች ጋር የንግድ ልውውጥ ታደርግ እንደነበር ተነግሯል።
የአክሱም ስልጣኔ የምስራቅ አፍሪካ እና የአረብ አካባቢዎችን እንደ አውሮፓውያኑ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ80 ዓመተ ዓለም እስከ 825ዓ.ም. ድረስ የተቆጣጠረ ሲሆን ይህም ከሮም ከፋርስ እና ቻይና ስልጣኔ ጋር እኩል የሚለካ ነው።
ይህች ቀዳሚ የስልጣኔ ምንጭ የሆነች ከተማ በኢትዮጵያውያን ዘንድ በታሪክ እንደማትታወቅ የገለፁት የሜሪላንድ ባልቲሞር ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ከተማዋ ከአከሱም ስልጣኔ በፊት የነበረች ናት ብለዋል።
በአፍሪካ ውስጥ ትልቁ ስልጣኔ እንደሆነም ነው በጥናታችን አረጋግጠናል ያሉት፡፡
‘ቤተ ሳማቲ’ የሚባለው ይህ ቦታ ትናንሽ ሕንፃዎችን ፣ ቤቶችን እና ባዛሊካ ተብሎ የሚታወቅ አንድ ትልቅ አራት ማዕዘን ቅርፅ ያለው ሕንፃንም የያዘ ነው። ይህ አራት መዓዘን ህንፃ በሮማ ግዛት ውስጥ በመጀመሪያ ለሕዝብ አስተዳደር እና ለፍርድ ቤቶች ፣በኋላ ላይ ደግሞ የክርስትና አምልኮ ቦታዎች ሆነው ያገለግሉ ነበር ፡፡
የአክሱም ስልጣኔ እንደ ግብጽ ግሪክና ሮም ስልጣኔ የበለጠ እንዲታወቅ እንሰራለን ብለዋል የባልቲሞር ተመራማሪዎች ፡፡
የአክሱም ስልጣኔ ከጥንታዊ ስልጣንዎች አንዱና ጠንካራው መሆኑን ማሳወቅ ቀዳሚ ስራቸው እንደሆነም ገልጸዋል ፡፡
እንደ ዴይሊ ሜል ዘገባ በቤተ ሳማቲ ከተገኙ ግኝቶች መካከል የወርቅ ቀለበቶች የነበሩ ሲሆን ዲዛይኑ በሮማ ስልጣኔ ዘመን የነበሩትን ይመስላል ፡፡
በአጠቃላይ አክሱም ስልጣኔና የተገኘችው ከተማ አካባቢው ቀደምት የስልጣኔ ቦታ መሆኑን እንደሚያመለክት የተገለጸ ሲሆን በአካባቢው ከፍተኛ የንግድ ለውውጥ መኖሩንም ያሳያል ተብላል ፡፡
ምንጭ፡- ዴይሊ ሜይል