በዓመት ከ700 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በስኮላርሽፕ የምትቀበለው አውስትራሊያ አዲስ ህግ አውጥታለች
ዩንቨርሲቲዎች ከመስፈርቱ ውጪ ተማሪዎችን ከመላው ዓለም መቀበላቸው አዲስ ህግ እንዲወጣ ምክንያት ሆኗል ተብሏል
ሀገሪቱ በሚቀጥለው ዓመት 270 ሺህ ተማሪዎችን ብቻ በስኮላርሽፕ መልኩ እንደምትቀበል አስታውቃለች
በዓመት ከ700 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በስኮላርሽፕ የምትቀበለው አውስትራሊያ አዲስ ህግ አውጥታለች፡፡
አውስትራሊያ በዓለማችን ካሉ ሀገራት መካከል በየዓመቱ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የስኮላርሽፕ አመልካቾችን በመቀበል ትታወቃለች፡፡
ሀገሪቱ አሁን ላይ ከመላው ዓለማችን ሀገራት 717 ሺህ ተማሪዎችን ተቀብላ በማስተማር ላይ ስትሆን በቀጣይ በምትቀበላቸው ተማሪዎች ዙሪያ ያላትን ፖሊሲ እንደምትከልስ አስታውቃለች፡፡
የአውስትራሊያ ዩንቨርሲቲዎች በየዓመቱ 24 ቢሊዮን ዶላር ከስኮላርሽፕ ገቢ በማግኘት ላይ ሲሆኑ የትምህርት መስፈርቶችን የማያሟሉ ተማሪዎች በስኮላርሽፕ መልኩ ወደ ሀገሪቱ ገብተው መገኘታቸው ተገልጿል፡፡
በአውስትራሊያ ቦታቸውን ለአልሚዎች አንሸጥም ያሉት “የዛሚት ቤተሰቦች”
ይህን ተከትሎም የሀገሪቱ መንግስት ዩንቨርሲቲዎች በየዓመቱ በሚቀበሏቸው ተማሪዎች ቁጥር ላይ ገደብ የሚጥል ረቂቅ ፖሊሲ እንዳዘጋጀ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በዚህ ረቂቅ ህግ መሰረትም የመንገስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በየዓመቱ በስኮላርሽፕ የሚቀበሏቸውን ተማሪዎች ብዛት ወደ 270 ሺህ ዝቅ እንዲያደርጉ ይገደዳሉ፡፡
የሀገሪቱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበር በበኩሉ መንግስት ያወጣውን አዲስ ገደብ ትክክል አለመሆኑን ገልጾ ረቂቅ ፖሊሲው የኢኮኖሚ አሻጥር ነው ሲል ተቃውሟል፡፡
አዲሱ የአውስትራሊያ ከፍተኛ ትምህርት ስኮላርሽፕ አመልካቾን የሚገድበው ረቅቅ ፖሊሲ ሀገሪቱን በየዓመቱ አራት ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ እና 22 ሺህ ሰራተኞችን ስራ የሚያሳጣ እንደሚሆን በዘገባው ለይ ተጠቅሷል፡፡