የቻይና ጦር ጄቶች የአውስትራሊያ ባህር ኃይል ሄሊኮፕተርን አዋክበዋል ነው የተባለው
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ፤ የቻይና የጦር ጄቶች የሀገሪቱን ሄሊኮፕተር ማዋከባቸውን ተከትሎ ተግባሩን “ተቀባይነት የሌለው” ሲሊ ተቃውሞዋቸውን አሰምተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቃውማቸውን ያሰሙት የቻይና ጦር ጄቶች በዓለም አቀፉ የውሃ ክልል ላይ በማለፍ ላይ የነበሩ የአውስትራሊያ ሄሊኮፕተሮች ላይ ሆን ብለው እሳት ለቀዋል የሚል ሪፖርት መቅረቡን ተከትሎ ነው።
የቻይና ጦር ጄቶች ምን አደረጉ?
የአውስትራሊያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ከሆነ MH60R ሲሃዋክ ህሊኮፕተር ባሳለፍነው ቅዳሜ በቢጫ ባር ላይ በመብረር ላይ እያለ የቻይና J-10 የጦር ጄት ከመቶ ሜትሮች ከፍታ ላይ ሆን ብሎ ወደ ሄኪኮፐተሩ እሳት ለቋል።
የመከላከያ ሚኒስትር ሪቻርድ ማርልስ ትናንት በጉዳዩ ላይ በሰጡት ማብራሪያም፤ የቻይና የጦር ጅት እሳቱን የተለቀቀው ከሄኪፖተሩ አናት 60 ሜትር ከፍታ እና ከፊትለፊቱ 300 ሜትር ርቀት ውስጥ ነው።
ይህም አብራው ከእሳቱ እንዳይመታ የራሱን እርምጃ ለመውሰድ እንዳስገደደውም ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።
በክስተቱ በሰው ላይም ይሁን በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም እሳቱ ሄሊኮፕተሩን አግኝቶ ቢሆን ኖሮ የሚያስከትለው አደጋ የከፋ እንደነበረም ነው የመከላከያ ሚኒስትሩ የተናገሩት።
የአውስትራሊያ የጦር ኃይሎች ከቻይና ትንኮሳ በተቃጣባቸው ሰዓት በዓለም አቀፍ የውሃ እና የአየር ክልል ላይ እንደነበሩ እና ተመድ በሰሜን ከሪያ ላይ የጣለው ማዕቀብን ተግባራዊነት ለማረጋገጥ ሲንቀሳቀሱ እንደነበረም ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።
ይህንን ተከትሎም የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ፤ “ተግባሩ ሙያዊ ያልሆነ እና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ለቻይና ግልፅ አድርገናል” ብለዋል።
አንቶኒ አልባኔዝ፤ አክለውም አውስትራሊያ ያለባትን ስጋት ባሉት የዲፕሎማቲክ እና የወታደራዊ መስመሮች ሁሉ ማሳወቋን የገለጹ ሲሆን፤ ቻይና ግን እስካሁን በጉዳዩ ላይ ምላሸ አልሰጠችም ተብሏል።
በቻይና እና አውስትራሊያ መካከል አንዲህ አይነት ትንኮሳ ሲነሳ በስድስት ወራት ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ ነው የተባለ ሲሆን፤ በህዳር ወር ላይ በካናቤራ ሶናር የተባለ የቻይና አውዳሚ የጦር መርከብ በጃፓን ባህር ላይ በአውስትራያ ጠላቂ ዋናተኞች መርከብ ላይ ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በወቅቱ በሰጠው ምላሽ ሶናር የተባለ የጦር መርከባ ወደ ስፍራው መላኩን በማስተባበል፤ የደረስ ጉዳት የለም ማለቱ ይታወሳል።