የወታደሮቹን መጥፋት ተከትሎ የጋራ የጦር ልምምዱ እንዲቆም ተደርጓል
ከአሜሪካ ወታደሮች ጋር በልምምድ ላይ የነበሩ የአውስትራሊያ ወታደሮች ጠፉ።
አሜሪካ እና አውስትራሊያ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ በማድረግ ላይ እያሉ አራት የአውስትራሊያ ወታደሮች ጠፍተዋል።
አራቱ ወታደሮች በጦር ሂልኮፕተር ሆነው ልምምድ በማድረግ ላይ እያሉ ግንኙነታቸው መቋረጡ ተገልጿል።
- አሜሪካ፣ብሪታኒያ እና አውስትራሊያ ወታደራዊ ጥምረት ለመፍጠር የሚያስችላቸውን እቅድ ይፋ አደረጉ
- አውስትራሊያ ከአሜሪካ የምትገዛቸው የጦር መርከቦች የፓስፊክን የሃይል ሚዛን ይለውጡት ይሆን?
አውሮፕላኑ ኪውንስላንድ ግዛት ውስጥ ባለው ዉቂያኖስ ስለመከስከሱ መረጃ በመውጣት ላይ ነው ተብሏል።
የአውሮፕላኑን መከስከስ ተከትሎ በትንሹ አራት ወታደሮች ሞተዋል የተባለ ሲሆን የጋራ ወታደራዊ ልምምዱ በአደጋው ምክንያት ተቋርጧል።
ወታደሮቹ ሲያበሩት የነበረው ኤምአርኤች-90 የተሰኘው የጦር ሂልኮፕተርን ፍለጋው እንደቀጠለ ሮይተርስ ዘግቧል።
አሜሪካ እና አውስትራልያን ጨምሮ ከ30 ሺህ ወታደሮች የተሳተፉበት የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ለሁለት ሳምንት እንዲካሄድ ታስቦ ነበር።
የወታደራዊ ልምምዱ አላማው የቻይናን ተጽዕኖ በእስያ ለመመከት በሚል እየተካሄደ ነበር።
ወታደራዊ ልምምዱ የየብስ፣ የባህር እና የአየር ሀይል ልምምድን ያካተተ ነበር የተባለ ሲሆን ቻይና በእስያ እያደረገች ላለው መስፋፋት ትብብራቸውን ለማሳየት ያለመም ነበር ተብሏል።
አሜሪካ እና ብሪታንያ የቻይናን ወታደራዊ ግስጋሴ ለመግታት በሚል በአውስትራልያ ኑክሌር የታጠቁ ባህር ሰርጓጅ መርከቦችን የማሰማራት እቅድ እንዳላቸው ከዚህ በፊት ተናግረው ነበር።