አዘርባጃን ቀጣዩን የተመድ የአየር ንብረት ጉባኤ ልታዘጋጅ እንደምትችል ተገለጸ
ባኩ ታዘጋጅ ወይም አታዘጋጅ የሚለው ጉዳይ በዱባይ እየተካሄደ ባለው የክፕ28 ስብሰባ ላይ ድርድር እየተካሄደበት ነው
ኮፕ29ን ማን ያዘጋጀው የሚለው ውሳኔ ሩሲያ ማንኛውም የአውሮፖ ሀገር እንዳያዘጋጅ እንደምትቃወም መግለጿን ተከትሎ ቀጣናዊ ወደሆነ የፖለቲካ ቅርቃር ውስጥ ገብቆ ቆይቷል።
አዘርባጃን ቀጣዩን የተመድ የአየር ንብረት ጉባኤ ልታዘጋጅ እንደምትችል ተገለጸ።
አዘርባጃን ከረጅም ጊዜ ተቀናቃኟ አርመንያ ጋር በጥያቄዋ ዙሪያ ስምምነት ላይ ከደረሰች በኋላ ቀጣዩን የተመድ የአየር ንብረት ጉባኤ(ኮፕ28) ለማስተናገድ አቅዳለች።
ሮይተርስ ዲፕሎማቶችን ጠቅሶ እንደዘገበው ሌሎች እጩዎችን የከለከሉት ሩሲያ እና ሌሎች ሀገራት ለባኩ ድጋፍ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ሞስኮ እስካሁን አቋሟን በይፋ አልገለጸችም።
ባኩ ታዘጋጅ ወይም አታዘጋጅ የሚለው ጉዳይ በዱባይ እየተካሄደ ባለው የክፕ28 ስብሰባ ላይ ድርድር እየተካሄደበት ነው።
ኮፕ29ን ማን ያዘጋጀው የሚለው ውሳኔ ሩሲያ ማንኛውም የአውሮፖ ሀገር እንዳያዘጋጅ እንደምትቃወም ወይም ቬቶ እንደምታደርግ መግለጿን ተከትሎ ቀጣናዊ ወደሆነ የፖለቲካ ቅርቃር ውስጥ ገብቆ ቆይቷል።
አዘርባጃን ባለፈው ሀሙስ እለት ተቀናቃኟ አርመንያ ባኩ ቀጣዩን ጉባኤውን እንድታካሂድ መፍቀዷን አረጋግጣለች።
የኮፕ ስብሰባን ለማስተናገድ የተመድ የምስራቅ አውሮፖ ቡድን ሀገራት ሙሉ ድጋፍ ያስፈልጋል።
የአዘርባጃን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አይካን ሀጂዛዳ "ከአብዛኛው ሀገራት(ከምስራቅ አውሮፕ ህብረት) ድጋፍ አግኝተናል። ሩሲያም ጥያቄያችንን ደግፋዋለች" ብለዋል።
ነገርግን ሩሲያ አቋሟን እስካሁን ይፋ አላደረገችም።
አዘርበረጃን የጋዝ እና ነዳጅ አምራች እና የኦፔክ ፕላስ ማህበር አባል ነች።
አንዳንድ የኮፕ28 የልኡካን ቡድኖች የአለምን የአየር ንብረት ድርድር ለሁለተኛ ጊዜ በነዳጅ አምራች ሀገራት መካሄዱ ላይ ጥያቄ አንስተዋል።
"ስጋታቸውን እንደረዳለን" ያሉት ቃል አቀባዩ ምንም እንኳን አዘርባጃን በጋዝ እና ነዳጆ ሀብታም ብትሆንም የኃይል ምንጭ የማብዛት ስትራቴጂካዊ ግብ እንዳላት ተናግረዋል።
አርመንያ ባኩ የኮፕ ጉባኤን እንድታስተናግድ የተስማማችው፣ የምስራቅ አውሮፖ የኮፕ ቢሮ አባል እንድትሆን ስለተፈቀደላት ነው።