ድርጅቱ በ2030 የ250 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት የመያዝ ውጥን ይዟል
ታዳጊ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን እንዲቋቋሙ የሚተጋው አልቴራ ፈንድ
በአረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ስምንተኛ ቀኑን ይዟል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየዓመቱ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የዓለም ሀገራት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎችን እና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት ጋር በመምከር ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ ጉባኤ ላይ ምድራችን በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚደርስ ጉዳትን መቀነስ የሚያስችሉ ምክክሮች እና ውይይቶች በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡
እስካሁን ከተወሰኑ ውሳኔዎች መካከል አልቴራ የተሰኘው የአየር ንብረት ለውጥ ኢንቨስትመንት አንዱ ነው፡፡
አፍሪካ ለአየር ንብረት ጉዳት ማካካሻ 87 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ተገለጸ
ይህ የአየር ንብረት ለውጥ ኢንቨስትመንት ባሳለፍነው አርብ የተወሰነ ሲሆን በ30 ቢሊዮን ዶላር ተመስርቷል፡፡
የዚህ ፈንድ ዓላማ በማደግ ላይ ያሉ እና ደሴቶችን ከአስከፊ የአየር ንብረት ለውጥ እንዲያገግሙ ዘላቂ ድጋፍ ማድረግ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
እንደ አረብ ኢምሬት ዜና አገልግሎት አልቴራ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ፈጠራዎችን እና ኢንቨስትመንቶችን ማበረታታት ሀገራት ከጉዳት እንዲያገግሙ ማገዝ ያስችላል፡፡
በፈረንጆቹ 2030 ለይም የፈንዱ አጠቃላይ ሀብት 25 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል የተባለ ሲሆን ዋነኛ የዓለማችን የኢንቨስትመንት ትኩረት ሆናልም ተብሏል፡፡