በኮፕ28 ወደ ተግባር እንዲገባ የተወሰነው ለአየር ንብረት ካሳ ፈንድ ዝርዝር ምን ይዟል?
አረብ ኢምሬትስ ለፈንዱ 100 ሚሊዮን ዶላር ለማዋጣት ቃል ገብታለች
በኮፕ28 በማድግ ላይ ላሉ ሀገራት የሚውል 'የአየር ንብረት ፈንድ' እንዲንቀሳቀስ ስምምነት ላይ ተደርሷል
በአረብ ኢምሬትስ ዱባይ እየተካሄደ በሚገኘው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (ኮፕ28) በማድግ ላይ ላሉ ሀገራት የሚውል 'የአየር ንብረት ፈንድ' እንዲንቀሳቀስ ስምምነት ላይ መደረሱ ይታወሳል።
የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ሴክሬታሪያት በኪሳራ እና ጉዳት ፈንድ አተገባበር ላይ የተሳታፊዎችን የመጨረሻ ውሳኔ ዘርዝር ይፋ አድርጓል።
በውሳኔው መሠረት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ስምምነት ተዋዋይ ወገኖች ለፈንዱ አስተዳደራዊ ዘሰራር ላይ ተስማምተው በአዲስና ገለልተኛ ጽሕፈት ቤት በኩል እንዲተዳደርና ፍንዱንም በዲሬክተሮች ቦርድ ቁጥጥር እንደሚደረግበት ከስምምነት ተደርሷል።
ፈንዱን እንደ መካከለኛ ፋይናንሺያል ፈንድ በአለም ባንክ ለአራት ዓመታት ጊዜያዊ ነት ንዲመራው ተጠይቋል። ፈንዱን የሚያገለግለው በአለም ባንክ በተዘጋጀ አዲስ እና ገለልተኛ ሴክሬታሪያት ነው።
ምክር ቤቱ የሁሉም አካላት ፍትሃዊ እና ሚዛናዊ ውክልና ያለው ግልጽነት ባለው የአመራር ስርዓት እንደሚመራ እና 26 አባላት ይኖሩታል የተባለ ሲሆን 12 ያደጉ ሀገራት፤ 14 ደግሞ ከታዳጊ አገሮች ነው።
በኮፕ28 በማድግ ላይ ላሉ ሀገራት የሚውል 'የአየር ንብረት ካሳ ፈንድ' እንዲንቀሳቀስ ስምምነት ላይ መደረሱ ይታወሳል።
አረብ ኢምሬትስ ለፈንዱ 100 ሚሊዮን ዶላር ለማዋጣት ቃል ገብታለች።
የኮፕ28 ፕሬዝደንት ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት ባደረጉት ጥሪ ጀርመን 100 ሚሊዮን ዶላር፣ እንግሊዝ 50 ሚሊዮን ዶላር፣ ጃፖን 10 ሚሊዮን ዶላር እና አሜራካ 17.5 ሚሊዮን ዶላር ለፈንድ ለማዋጣት ቃል ገብተዋል።