ከጊዜ ወደ ጊዜ በባህር ዳር እየተፈጸመ ያለው የቦንብ ጥቃትና ግድያ ገጽታ የሚያበላሽ ነው ተብሏል
የባህር ዳር ከነማ ደጋፊዎች ማንነታቸው አልታወቀም በተባሉ አካላት ቦምብ ተወረወረባቸው።
ደጋፊዎቹ ግንቦት 18፤ 2015 ዓ.ም. ከቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ወደ ሀዋሳ ለመጓዝ አውቶብስ ውስጥ ሲገቡ ጥቃቱ እንደተፈጸመባቸው ተነግሯል።
በጥቃቱ 23 የክለለቡ ደጋፊዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት በመድረሱን የባህር ዳር ከንቲባና የክለቡ የቦርድ ሠብሳቢ ድረስ ሳህሉ ተናግረዋል።
የጥቃቱ ሰለባዎች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው ተብሏል።
የጸጥታ አካላት ወንጀል ፈጻሚዎችን ተከታትለው ለህግ ያቀርባሉ ተብሏል።
ከንቲባው ከጊዜ ወደ ጊዜ በከተማዋ ላይ እየተፈጸመ ያለው የቦንብ ጥቃትና ግድያ "ጸረ-ሠላም እንቅስቃሴ" ነው ያሉት ሲሆን፤ ሊወገዝ እንደሚገባም አሳስበዋል።
ህብረተሰቡ የከተማዋን ሠላም የሚያውኩ አካላትን በመለየት ለህግ እንዲቀርቡ ማድረግ ይገባዋልም ብለዋል።