የግብፁ ኮኮብ ሞሃመድ ሳላህ “በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ ከፍተኛ የሆነ ሳምንታዊ ደሞዝ” ጠየቀ
ተጨዋቹ አሁን ላይ በሳምንት 200 ሺ ፓውንድ እንደሚከፈለው የእንግሊዙ ጋዜጣ ‹ዘ-ሚረር› ዘግቧል
ሳላህ ከሊቨርፑል ጋር ለመቆየት የጠየቀው ሳምንታዊ ደሞዝ “ግማሽ ሚሊዮን ፓውንድ” ነው
የግብፁ ኮኮብ ሞሃመድ ሳላህ ከሊቨርፑል ጋር ለመቆየት ግማሽ ሚሊዮን ፓውንድ ሳምንታዊ ደሞዝ ጠየቀ፡፡
ሳላህ ከሊቨርፑል ጋር ያለውንና በሰኔ 2023 የሚያበቃውን ኮንትራት ውል ለማደስ ድርድር በማድረግ ላይ መሆኑን የእንግሊዙ ጋዜጣ ‹ዘ-ሚረር› ዘግቧል፡፡
‹ዘ-ሚረር› በዘገባው ከሊቨርፑል ጋር ያለውን ውል ለማደስና ለመቆየት “ግማሽ ሚሊዮን ፓውንድ ሳምንታዊ ደሞዝ” እንደሚያስፈልገው ጠይቋል ብሏል፡፡
ሳላህ የጠየቀው የክፍያ መጠን በክለቡም ሆነ በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ “ከፍተኛ ነው” እንደዘገባው፡፡
የክለቡ ከፍተኛ ተከፋይ ከሆነው ሆላንዳዊው ቨርጂል ቫን ጂክ ጋር ሲነጻጸር እንኳ ከእጥፍ በላይ ነው ሳላህ የጠየቀው የገንዘብ መጠን፡፡
ሆላንዳዊው ተከላካይ ቨርጂል ቫን ዳይክ 220 ሺ ፓውንድ ሳምንታዊ ደሞዝ እንደሚቀበል ይታወቃል፡፡
ሳላህ ያቀረበው የክፈያ መጠን እንደሚከፈለው እርግጠኛ ለመሆን ባይቻልም፤ ከሊቨርፑል ጋር ባለው ውል መሠረት አሁን ላይ በሳምንት 200 ሺ ፓውንድ የሚቀበል ሲሆን ውሉን ካደሰ የክለቡ አስተዳደር እንደሚያሳድግለትና ከፍተኛ ተከፋይ እንደሚያደርገው ይጠበቃል፡፡
የሳላህ ጥያቄን ተከትሎ እንደ ሪያል ማድሪድ እና ፒኤስጂ የመሳሰሉ የአውሮፓ ክለቦች ተጨዋቹን ለመውሰድ ፍላጎት ያሳዩ ክለቦች ናቸው፡፡
የክለቦቹ ሳላህን የራስ የማድረግ ፍላጎትም ታድያ የሊቨርፑሉ አስልጣኝ ጀርግን ክሎፕ ትልቅ ጭንቀት ውስጥ ሳይከታቸው እንዳልቀረ ይነገራል፡፡
ከሳላህ በተጨማሪ የብራዚሉ ግብ ጠባቂ አሊሰን ቤከር፣ የአገሩ ልጅ ፋቢንሆ ሆላንዳዊው ተከላካይ ቨርጂል ቫን ዳይክ፣ እንግሊዛዊው ተከላካይ አሌክሳንደር አርኖልድ እና ስኮትላንዳዊው አንዲ ሮበርትሰን ከክለቡ ጋር ያላቸውን ውል እስካሁን ያላደሱ ተጫዋቾች ናቸው፡፡