የራጃ ካዛብላንካ እና የቲፒ ማዜምቤ ጨዋታን እንዲመራ ተመርጧል
ባምላክ ተሰማ የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታን እንዲመራ ተመረጠ
ኢትዮጵያዊው የመሐል ዳኛ ባምላክ ተሰማ የሞሮኮው ራጃ ካዛብላንካ ከኮንጎው ቲፒ ማዜምቤ የሚያደርገውን የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ እንዲመራ ተመርጧል።
የሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታ በመጪው አርብ ካዛብላንካ ላይ የሚደረግ ሲሆን የመልሱ ጨዋታ ደግሞ ከ15 ቀናት በኋላ ቅዳሜ መጋቢት 7 ሉሙምባሺ ላይ ይደረጋል፡፡
በአምላክ ከረዳቶቹ ተመስገን ሳሙኤልና ለሚ ንጉሴ ጋር በመሆን የግብፁ ዛማሌክና የዛምብያው ዜስኮ ከወራት በፊት ያደረጉትን ጨዋታ መርቷል፡፡
ሆኖም በዚህኛው የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ረዳቶቹ ሆነው ጨዋታውን የሚመሩት ዳኞች እነማን እንደሆኑ እስካሁን ድረስ አልታወቁም፡፡
ከወዲሁ በርካታ ተጠባቂ ጨዋታዎች ያሉት ይሄ ውድድር በሩብ ፍፃሜው አልሃሊን ከማሜሎዲ ሰንዳውንስ፣ ዋይዳድ ካዛብላንካን ከኤታል ደ ሳህል፣ ዛማሌክን ከኤስፔራንስ ደቱኒዝ እና ራጃ ካዛብላንካን ከቲፒ ማዘንቤ አገናኝቷል፡፡